Winamp Logo
ዜና መጽሔት | Deutsche Welle Cover
ዜና መጽሔት | Deutsche Welle Profile

ዜና መጽሔት | Deutsche Welle

Amharic, News, 1 season, 232 episodes, 2 days, 39 minutes
About
ዝግጅቱ ዜና ትንታኔ እና ዘገባዎች ይቀርብበታል።
Episode Artwork

የጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መፅሔት

2/5/202418 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

በተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

በአማራ ክልል ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ የውስጥ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበት ሁኔታ አለመመቻቸቱን እንደሚያሳይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ተናገሩ። የድንጋጌው መራዘም የሕዝቡን ችግር እንደማይቀርፍ ሌሎች ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችም ይናገራሉ።
2/5/20244 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

እየተባባሰ የመጣው የመንገድ ላይ ጥቃት

ለወትሮው አንጻራዊ ደህንነት ይስተዋልባቸው የነበሩት ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ፣ ወልቂጤና ቡታጅራ መንገዶች አሁን ላይ አሽከርካሪዎች በሥጋት ፤ መንገደኞች በፀሎት የሚጓዙባቸው መስመሮች ሆነዋል ነው የሚባለው ፡፡
2/5/20243 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታው

አማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ የተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ ም ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አፅድቋል፡፡ ምክር ቤቱ የጊዜውን መጠናቀቅ ተከትሎ ትናትን ባደረገው ልዩ ስብሰባ አዋጁ ለሌላ 4 ወራት እንዲራዘም ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡
2/3/20244 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙን ለአብዛኞቹ አሳሳቢ ሆኗል

2/3/20244 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

የጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

2/2/202419 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

የሐሙስ ጥር 23 ቀን፣ 2016 ዓ. ዜና መጽሄት (ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ታሰሩ ፣ አዋሽ አርባ ታስረው የነበሩ የምክር ቤት አባላት ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ፤ ሕወሓት የ41 ቀናት ስብሰባ አጠናቀቀ..)

2/1/202426 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

ዓለም አቀፍ የእርዳታ ጥሪ ዘመቻ

`` ወደ አፍሪቃ ሕብረት፣ ኢጋድ፣ የአውሮጳ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግስታት፣ አሜሪካ፣ ታላቋ ብሪታንያና ለሌሎች 30 የሚሆኑ የረድኤት ድርጅቶች ፊርማ በማሰባሰና በቀጥታ ወደ መንግስታቱና ተቋማት ኢ ሜይል በመጻፍ ረድኤት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርጉ ለማሳሰብ ነው የዘመቻው ዓላማ።`` ወይዘሪት ባትሰባ ሰይፉ
2/1/20244 minutes
Episode Artwork

የጥር 22 ቀን 2016 የዜና መጽሄት

1/31/202417 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

“የአንቅስቀሰሴ ገደብ” በኦሮሚያ ክልል

“ያው ሰውም እየተንቀሳቀሰ አይደለም፡፡ የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪም የለም፡፡ የጸጥታ ኃይሎች እያስገደዱ ብቻ ሰው መናሃሪያ አከባቢ ስሰባሰብ በግዳጅ ከሚሄዱት አንድ ሁለት ተሸከርካሪዎች ውጪ ምንም እንቅስቃሴ የለም፡፡“ ከምዕራብ ሸዋ ዞን አደኣ በርጋ ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ
1/31/20243 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የጣልያን አፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ በሮም

ጉባኤውን ተrተርሰው የጣልያን ጋዜጦች በርካታ ጉዳዮች የዘገቡ ቢሆንም በተለይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትርና የሶማልያው ፕረዚደንት ለማነጋደር ሙከራዎች እንደነበረ፤ የሶማልያው ፕረዚደንት ለአንድ የጣልያን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫም ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የወደብ ኪራይ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ቀጠናውን የሚያተራምስ በማለት አጣጥለውታል።
1/31/20244 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

የጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መጽሔት

1/30/202418 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም.

1/26/202417 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

«በኦሮሚያ መንግሥት በሚያካሂዳቸው ዘመቻዎች ንጹሃን ዜጎች የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው»

ስለመግለጫው አስተያየታቸውን የሰጡት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ፤ በተለይም በወረዳው ጉቢሶ ቀበሌ ተፈጽሟል ያሉት የአየር ላይ ጥቃት በርካታ የቤት እንስሳት ማለቃቸውንም ገልጸዋል፡፡ መጠነ ሰፊ ጉዳቶች የደረሱት በሰላሌ እና ደቡብ ምዐወራብ ሸዋ ዞን ነውም ብለዋል፡፡ጥቃቱ የተፈጥሮ ሃብትንም ያወደመ ነበር” ነው ያሉት፡፡
1/26/20243 minutes, 8 seconds
Episode Artwork

"ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠት የስምምነቱ አካል ነው" በኢትዮጵያ የሶማሌላንድ ተወካይ

እአምባሳደር አብዱላሂ ሶማሊያን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው አለመረጋጋት ምንጭ አድርገው ከሰዋል።«በአንጻሩ ሶማሊላንድ ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ ድርሻ አላት። "ኢትዮጵያም፣ ድንበሯም እንዲከበር እንጠብቃለን። ሁለተኛ ፣ ሶማሊላንድ በሕግ የፀና እውቅና ያለው ግዛት ሆኖ መታወቅ አለበት። ሶማሊላንድ አልሸባብን እና ሽብርተኝነት ትዋጋለች"ብለዋል።
1/26/20243 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

የጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

1/25/202422 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የረቡዕ ጥር 15 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽኄት

1/24/202417 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

የምግብ እጥረት በአበርገሌና በፃግበጂ ወረዳዎች

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአካባቢው ታጣቂዎችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በነበረ ጦርነት ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎች ርዳታ እየቀረበልን አይደለም አሉ ። የአካባቢው ባለሥልጣናት ርዳታ እየተሰጠ ነው ሲሉ አስተባብለዋል ።
1/24/20244 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፤ ጥር 14 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ማክሰኞ

1/23/202418 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

የወጣት ሥራ አጥነት እና ሕገ-ወጥ ስደት በትግራይ

በትግራይ የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ሕገ-ወጥ ስደት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ። የኢትዮጵያ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በመጀመርያ ዙር በትግራይ ለሚገኙ 2 ሺህ ወጣቶች የስልጠናና ፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩ፥ ከዚህ ውጭም የተለያዩ ፕሮጀክት እየተገበረ እንደሚገኝ አስታውቋል።
1/23/20243 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

ሰላም እና የሲቪክ ድርጅቶች አስተዋጽዖ

ኢትዮጵያ ውስጥ ጠባብ የፖለቲካ ምህዳር ቢኖርም ዘላቂ ሰላምን ፣ ተስማምቶ መኖርን እና አብሮነትን ለማጠናከር እና በሰላም ግንባታ ላይ ለመሥራት መቋቋሙን ስርየት ለሁሉም የተባለ ሲቪክ ድርጅት ገለፀ። ሲቪክ ድርጅቱ በማህበረሰብ ውይይት ፣ በትምህርት እና በምርምር ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ለማገዝ እንደሚንቀሳቀስ ገልጿል።
1/23/20242 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም.

1/22/202420 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል የጥምቀት በዓል እንዴት አለፈ?

የጥምቀት በዓል አከባበር በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ሰፊ ስጋት አሳድሮ ነበር፡፡ የክልሉ መንግሥት እንዳለው ግን በዓላቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው ተጠናቅቀዋል፡፡ያም ሆኖ በአንዳንድ የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም አካባቢዎች በዓሉ በቤተክርስቲያናት አጥር ግቢ ብቻ መከበሩንነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡
1/22/20244 minutes, 17 seconds
Episode Artwork

ሰሚ ያጣው የደቡብ ዲዛይን ፣ ግንባታና ቁጥጥር ድርጅት ሠራተኞች አቤቱታ

የሠራተኞቹ ተወካዮች «ድርጅቱ በሠራተኛው ጥረት ትርፋማ በመሆን በርካታ ሀብቶችን አፍርቷል።የሚዘጋውም በኪሳራ ሳይሆን በመንግሥት ትዕዛዝ ነው ፡፡ በመሆኑም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156 እና በህብረት ሥምምነት መሠረት ተገቢው ጥቅማ ጥቅሞች እንዲከበሩልን እንፈልጋለን ፡፡ አማራጭ የሥራ ዋስትናችንንም ሊያረጋግጥ ይገባል “ ብለዋል ፡፡
1/22/20243 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀምና ትችቱ

የውሉ ፈራሚዎች ስምምነቱ እየተገበሩ አይደለም በማለት የሚተቹ አቶ ብርሃነ አደራዳሪ የነበሩ አካላት ለምን የውሉne ትግበራ በቅርበት አይከታተሉም በማለት ይወቅሳሉ። የሰላም ስምምነቱ ተፈራራሚዎች የጠበንጃ ድምፅ ከማስቀረት ባለፈ የሚጠበቁ በርካታ ተግባራት አልከወኑም በማለት የሚወቅሱ ደግሞ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሲቪክ ማሕበራት ሕብረት ነው።
1/22/20243 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ፣የባሕር በር የማግኘት ጥረቷ እና የሀገራት ምላሽ

ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር በቅርቡ የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት የባሕር በር ማግኘት የምትችልበት የትብብርና የአጋርነት ስምምነት መሆኑ ሊታወቅ እንደሚገባ አስታወቀች። ኢትዮጵያ ይህን ያለችው የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ሀገራቸው የትኛውም ሀገር ሶማሊያንም ሆነ ደኅንነቷን ስጋት ውስጥ እንዲጥል አትፈቅድም ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
1/22/20244 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

የጥር 10፣2016 ዜና መፅሔት

1/19/202422 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢው የሰብአዊ መብት ጥሰት በጋሞ ዞን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ከአስተዳደራዊ መዋቅር ጋር ለተያያዙ አለመግባባቶች አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ ፡፡ ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአርባ ምንጭ አስተዳደርና በዙሪያው ቀበሌ የተነሱ የአስተዳደር ጥያቄዎች አሁንም ለሰዎች ሞትና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት እየሆነ ይገኛል ብሏል ፡፡
1/18/20242 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የቤሕነን አመራር ውዝግብና ክስ

የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን)ፓርቲ ከሐምሌ ወር መጨረሻ አንሰቶ የታሰሩ 6 ሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴን ጨምሮ ከ20 በላይ አባላቱ አሁንም ድረስ እንዳልተፈቱ ገለጠ ። ፖለቲከኞቹ የታሠሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ከክልሉ መንግስት ጋር በሰላምና ልማት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት በሚል ስምምነት መፈራራማቸውን በመቃወማቸውን ነው ተብሏል።
1/18/20243 minutes, 16 seconds
Episode Artwork

የሐሙስ ጥር 9 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. ዜና መጽኄት

1/18/202424 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

የጥር 8፣2016 ዜና መፅሔት

1/17/202419 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

የማክሰኞ ጥር 7 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. ዜና መጽሄት

1/16/202418 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

ህወሓት በረዥም ስብሰባ ተጠምዷል

በትግራይ ክልል የከፋ ሁኔታ ባለበት የህወሓት አመራር በረዥም ስብሰባ ተጠምዶ ይገኛል በማለት ተቃዋሚዎች ተቹ። የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት፣ ነባር የፓርቲው አመራር፣ የትግራይ ወታደራዊ መሪዎች እና ሌሎች እየተሳተፉበት የሚገኘው ሰብሰባ እስካሁን መቋጫ አላገኘም። የክልሉ አስተዳደር የሚሰነዘርበትን እነዚህን ክሶች ውድቅ አድርጓል ።
1/16/20243 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ

1/15/202420 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

የጀርመን ገበሬዎች እና የጣምራዉ መንግሥት ዉዝግብ

የጀርመን ገበሪዎች ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት መጀመርያ በጀርመን በተለያዩ ከተሞች መንግሥት የሚሰጠን ድጎማ ቀንሶብናል ሲሉ ገበሪዎች የአደባባይ ተቃዉሞ አድርገዋል። ጀርመን ከባቡር አሽከርካሪ እስከ አራሽ ገበሪ ለተቃዉሞ አደባባይ በመዉጣታቸዉ፤ ጀርመን በተቃዉሞ ሙድ ዉስጥ ገብታለች ሲሉ የተለያዩ ጋዜጦች በርዕስነት ይዘዉ ዘግበዋል።
1/15/20244 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሕገ - መንግሥት ጥሰት አቤቱታ ቀረበበት

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያወጣው ደንብ ቁጥር 4/2016 የኢፌዴሪን ሕገ - መንግሥት አራት አንቀጾችን የሚቃረን ነው በሚል የሕገ- መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ጉዳዩ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ለሕገ - መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የዳኝነት አቤቱታ ቀረበ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ደንብ ለምን አወጣው ?
1/15/20243 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢ የወባ ወረርሽኝ በዎላይታ ዞን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያንዣበበው የሞት ጥላ በቀላሉ የሚገፈፍ አይመስልም ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በወረዳው እየተባባሰ የመጣው የወባ ወረርሽኝ አሁን ላይ የብዙዎችን በር እያንኳኳ ፤ በርካቶችንም የአልጋ ቁራኛ እያደረገ ይገኛል።
1/15/20244 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚዘጋው፣ የሚገደበው ኢንተርኔት እና ያስከተለው ኪሳራ

ኢትጵጵያ ውስጥ ግጭቶች ሲከሰቱ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉም ይሁን በከፊል ተዘግቶ ያውቃል ፣ አሁንም በአማራ ክልል አገልግሎቱ እንደተዘጋ ነው። መንግሥት ጉዳትን ለመቀነስ እና የሀገር ደህንነትን ለመጠበቅ በሚል ኢንተርኔትን ሲዘጋ ቢስተዋልም ጥናቶች "ኢንተርኔትን መዝጋት የሚነሱ አመጾችን በማስቀረት በኩል ጠቀሜታቸው እምብዛም " መሆኑ ተገልጿል።
1/15/20244 minutes, 25 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ጥር 3 ቀን 2016 ዓ.ም አርብ

1/12/202422 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

በትግራይ በጦርነት የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች ጥሪ

ጦርነቱ ከቆመ 15 ወራት ቢቆጠሩም፥ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች አሁንም ወደቀዬአቸው አልተመለሱም። በሽረ፣ ዓብይአዲ፣ መቐለ ያሉ ተፈናቃዮች መንግስት ወደቀዬአቸው እንዲመልሳቸው እንዲሁም ዓለምአቀፍ ለጋሾችም የእርዳታ እጃቸው እንዲዘረጉላቸው ጥሪ አቀረቡ። የትግራይ ክልል ከ1 ሚልዮን በላይ ተፈናቃዮች በመጠልያዎች ይገኛሉ።
1/12/20243 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል ከ100 ሺህ በላይ ህፃናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል

በሰሜን ጎንደር ዞን በተለይም ጃንአሞራ ወረዳ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳትና በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናገሩ። መንግስት በአፋጣኝና በተከታታይ እርዳታ ካላቀረበ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር እርዳታ ለማድረስ እንቅፋት እየፈጠረ ነዉ ባይ ነዉ።
1/12/20244 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቋም

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግስት ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የፈረመውን የፍላጎት ማሳያት የመግባቢያ ሰነድ እንደሚደግፍ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ይሁንና መንግስት አስቀድሞ በመሰል አወዛጋቢ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አለመወያይቱን በብርቱ ተችተዋል፡፡
1/12/20244 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

የጥር 2፣2016 ዜና መፅሔት

1/11/202424 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ማስተማር ሊጀምሩ ነዉ

ዩኒቨርስቱዎቹ ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ ያስታወቁት የፌደራሉ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንዲቀበሉ ከወሰነ በኋላ ነዉ።ወላጆች የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ትምህርት ለመጀመር አያስችልም የሚል ስጋት ያደረባቸው ሲሆን አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ ወደየዩኒቨርቲያቸው ለመሄድ ግራ እንደተጋቡ አስታዉቀዋል፡፡
1/11/20243 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የጥር 1 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መጽሔት

1/10/202419 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 30፣2016 ዜና መፅሔት

1/9/202420 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ታኅሳስ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ

1/8/202420 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

የጀርመን ገበሬዎች መንግሥትን በመቃወም አድማ መቱ

የጀርመን መንግሥት ለገበሬዎች የሚሰጠዉን የእርሻ ድጎማዎችን ለመቀነስ ያወጣውን ዕቅድ ተከትሎ የጀርመን ገበሪዎች በርሊን ላይ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ጀምረዋል። በመላ አገሪቱ የመንገድ መዘጋቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚሄዱ ተጓዦችን እያደናቀፈ ነዉ። መዲና በርሊን እምብርት ላይ ገበሪዎች የእርሻ ትራክተራቸዉን ይዘዉ አደባባይ ወጥተዋል።
1/8/20244 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የፍትህ ተደራሽነት ጥያቄ በደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች

የቀድሞው የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚታዩ ጉዳዮችን ለመመለከት ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት በሃድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ያስችል እንደነበር የሚያስታውሱት ጠበቃ አስፋው “ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚል በአዲስ ከተዋቀረ በኋላ ግን ሲሰጥ የነበረው የተዘዋዋሪና ምድብ ችሎት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡
1/8/20243 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነት ፣ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ስምምነቱን ውድቅ የሚያደርግ ነው ያሉትን ሕግ በፊርማቸው ማጽደቃቸውን ተናግረዋል። የፈረሙትን ሕግ ዓላማውን "አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን ብሎም የግዛት አንድነታችንን ለመጠበቅ" ያለመ ብለውታል። ዛሬ ፕሬዝዳንቱ ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ለመምከር ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል"
1/8/20244 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መፅሔት

1/5/202413 minutes, 55 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 25፣2016 ዜና መጽሔት

1/4/202424 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ታኅሳስ 24 ቀን 2016 ዓ.ም.

1/3/202418 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 23፣2016 ዜና መፅሔት

1/2/202419 minutes, 34 seconds
Episode Artwork

የታኅሳስ 22 ቀን 2016 ዜና መጽሔት

በኢትዮጵያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ቁጥራቸው ብቻ ሳይሆን አሰቃቂነታቸው ጭምር እየበረታ ነው። ሙሽራ ልጃቸው ተቃጥሎ የተገደለባቸው አባት “አመድ ነው ሰብስበን የቀበርንው” እያሉ ነው። በአዲስ አበባ የተለያዩ ወንጀሎች በመፈጸም የተጠረጠሩ ከ5 ሺሕ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የፌድራል መንግሥት በትግራይ የተከሰተው ድርቅ እና ረሐብን አስመልክቶ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሠ ቱሉ የሰጡትን መግለጫ እንዲያርም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጠየቀ። የብሪክስ መስፋፋት ተጽዕኖውን እንደሚያሳድገው ቢታመንም ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ለሀገራቸው በሚኖረው ፋይዳ ላይ ጥያቄ አላቸው።
1/1/202419 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

12/28/202324 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 17፣2016 ዜና መፅሔት

12/27/202318 minutes, 16 seconds
Episode Artwork

የማክሰኞ ታኅሣሥ 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. መጽኄተ-ዜና

12/26/202317 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

የታኅሳስ 15 ቀን 2016 ዜና መጽሔት

የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ አረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ (ባይቶና) ኪዳን ለሥር ነቀል ለውጥ የተባለ ጥምረት መሰረቱ። በአማራ ክልል በዋግሕምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በተከሰተ ድርቅ ከ85 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የየአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ገለጹ። በሐድያ ዞን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላልተቀጠሩ ሠራተኞች ደሞዝ ይከፍላሉ ሲሉ ነዋሪዎች ወነጀሉ።
12/25/202313 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 12፣2016 ዜና መፅሔት

12/22/202319 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

12/21/202325 minutes, 34 seconds
Episode Artwork

የታሕሳስ 10፣2016 ዜና መፅሔት

12/20/202318 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ማክሰኞ

12/20/202319 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

የአማራ ክልላዊ መንግስት የሰላም ጥሪዉን ማራዘሙ

የአማራ ክልላዊ መንግስት ዳግም ለ 7 ቀናት የሚቆይ የሰላም ጥሪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያስተላለፈው፣ ከዚህ በፊት የተሰተው የ7 ቀናት የሰላም ጥሪ በቂ ባለመሆኑ ነው ብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ውጊያዎች እንደነበሩና አሁንም እንደቀጠሉ ከየአካባቢው የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
12/19/20234 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የቀረበው ሹመት ፀደቀ

በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ሹመታቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ። አዲሷ ተሿሚ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ለሦስት ዓመታት ማግልገላቸው ተነግሯል።
12/19/20233 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

18 የሲቪክ ድርጅቶች ቁልፍ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ለምክክር ኮሚሽን አስገቡ

18 በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪክ ድርጅቶችን ያቀፈው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሕብረት በሀገራዊ ምክክሩ መነሳትና መታየት ያለባቸው እና ቁልፍ ያላቸውን አራት የሰብዓዊ መብት አጀምዳዎች ለብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አቀረበ። ሕብረቱ የ አናሳ የማህበረሰብ ክፍሎች ወይም ህዳጣን ማህበረሰቦች የፖለቲካ ውክልና እንዲኖራቸው የሚል ነዉ።
12/19/20234 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

በኦሮሚያ ክልል ግብርናን የማዘመን ጥረትና ፈተናው

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ግብርናውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምርትና ምርታማነቱን የማሳደግ ስራ እየተከወነ ነዉ። አርሶ አደሩ ከዚሁ ጥረት እየተጠቀመ መሆኑን ባይሸሽግም የግብርናዉን ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚፈትነዉ የአየር ጠባይ እና የግብዓቶች ዋጋ መናር ፈተናዉን እንዳከበደበት ይናገራል።
12/19/20234 minutes, 23 seconds
Episode Artwork

ከመኖርያ ቤታቸዉ የተባረሩት የፖለቲከኛዉ ባለቤት

በሽብር ተጠርጥረዉ የታሰሩት የፖለቲከኛ ታዬ ደንደአ ቤተሰብ ሲኖሩበት ከነበረው ቤት ውስጥ እንደወጡ ተናገሩ። የፖለቲከኛው ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ እንዳሉት ሐሙስ ታህሳስ 04 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ መንግስት የሰጣቸዉ መኖሪያ ቤት እስከነ እቃው ታሽጓል። ወ/ሮ ስንታየሁ ደጅ እንድንወድቅ ነተደርገናል ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
12/15/20234 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

የወጣቶች አፈሳ በሃድያ ዞን

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን የመንግሥት አመራሮችን ተችተዋል የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በጅምላ እየታፈሱ ነው፡፡ የወጣት ታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ወጣቶቹ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የመንግስት አመራሮች በመተቸታቸው ብቻ ለእሥር ተዳርገዋል፤ የግል ንብረቶቻቸውም በፀጥታ አባላት ተወስደውባቸዋል፡፡
12/15/20234 minutes, 6 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 4 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄት

12/14/202326 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የታኅሳስ 03 ቀን 2016 ዜና መጽሔት

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በምትገኘው አሙሩ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት 13 ሰዎች ሲገደሉ አራት መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከ20 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ዝቅ እንዳለ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ዛሬ ገልጸዋል። እነዚህን ጨምሮ አራት ርዕሰ ጉዳዮች ለዛሬ በዜና መጽሔት ይደመጣሉ።
12/13/202317 minutes, 55 seconds
Episode Artwork

የማክሰኞ ታኅሣሥ 2 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽሄት

12/12/202319 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

በኦሮሚያ ህብረተሰቡን መረጋጋት የነሳው ግጭት

በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ መንግስትና መንግስት ሸኔ ባለው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት የህብረተሰቡን የእለት ተእለት ህይወት መፈተኑን ቀጥሏል፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች በጸጥታ ችግሩ አለመረጋጋት ምክንያት ህይወታቸውን በተረጋጋ ሁኔታ መምራት ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡
12/11/20234 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

የሶማሌ ክልል የተረጋጋ አካባቢ ሆንዋል መባሉ

የሶማሌ ክልል ለችግሮቹ በፈጠረው ፖለቲካዊ መፍትሄ ነፃ ሆኖ መንቀሳቀስ ወደ ሚያስችል የተረጋጋ አካባቢ መለወጡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። ከዓመታት በፊት በጅግጅጋ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች ብሄርና ኃይማኖት ላይ አተኩረው የተፈፀሙ ጥቃቶች መንስዔ ፖለቲካዊና የወቅቱ አመራሮች ቀስቅሰዉት ነበር የተባለዉን ሁኔታ በመቀየር ችግሩ ተፈቷል።
12/11/20234 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ የሚገኙ የትጥቅ ግጭቶች ዘላቂ እና ሰላማዊ መፍትሔ እንዲበጅላቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድጋሚ ጠየቀ። ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች መፍትሔ እንዲያገኙ ድጋሚ ጥሪ ያቀረበው 75ኛው ዓመት የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ቀንን ተንተርሶ ባወጣው መግለጫ ነው።
12/11/20234 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መጽሄት

12/8/202318 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመር በአሶሳ

በአሶሳ ከተማ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች እንደገለፁት በተለይ ጤፍ፣ሽንኩርት፣ቡና እና ሌሎች ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ ነው፡፡ ፡፡ የክልሉ ንግድና የገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ገብረ ሀይል በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
12/8/20233 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ያማረረው የትራንስፖርት አገልግሎት

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የሚነገርለት የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር እልባት ያላገኘ እና እያደገ የመጣውን የከተማዋ ነዋሪዎች ቁጥርን ያላገናዘበ ነው በሚል ይተቻል። የከተማዋ ነዋሪዎች በመንገዶች መጨናነቅ መንገድ ላይ ከሚያቃጥሉት ጊዜ በተጨማሪ ትራንስፖርት ለመጠበቅም በቀን ውስጥ ሰዓታትን እንደሚያሳልፉ በምሬት ይገልጻሉ፡፡
12/8/20234 minutes
Episode Artwork

ለእሑድ ኅዳር 30 የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ

የፊታችን እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ሊካሄድ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ ለሌላ ጊዜ መራዘሙን አስተባባሪ ኮሚቴው አስታውቋል። ኮሚቴው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰልፉ ለሌላ ጊዜ የተላለፈው መንግስት አራት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴን ማሰሩን ጨምሮ «አሉታዊ» የተባሉ እርምጃዎች በመወሰዳቸው ነው ብሏል፡፡
12/8/20234 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

በአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዚዳታዊ ዕጩዎች ክርክር

በአሜሪካ ቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ለመወከል የቀረቡ ዕጩዎች የመጨረሻውን ክርክር ሰሞኑን በአላባማ አካሂደዋል።በመጭው የሀገሪቱ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ግን በአላባማው ክርክር አልተሳተፉም ተብሏል።
12/8/20233 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ ሐሙስ ኅዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም.

12/7/202325 minutes, 11 seconds
Episode Artwork

እሑድ በአዲስ አበባ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እና የገጠመው ስጋት

የፊታችን እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ጦርነት ይቁም ሰላም ይሰፈን በሚል መሪ ሃሳብ አዲስ አበባ ውስጥ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ መቅረቡ ተገለጸ። ሰልፉ የተጠራውም በፖለቲከኞች፣ ሲቪል ተቋማት እና በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ነው ተብሏል። ይሁንና የሰልፉ አዘጋጆች ከመንግስት ሰልፉ እንዳይካሄድ ማስፈሪሪያ ደርሶናል ይላሉ።
12/6/20233 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

በማንነት ላይ ያነጣጠር ጥቃት ቀጥሏል መባሉ

በኦሮሚያ ክልል በወለጋና በአርሲ ዞኖች ምእመኖቻቸዉ እና አገልጋዮቻቸዉ በታጣቂዎቸ በግፍ እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ገለፁ። ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ዘጠኝ ምእመኖች እንዲሁም በቄለም ወለጋ 9 አገልጋዮቿ መገደላቸዉን ተገልጿል።
12/6/20234 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢዉ የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ በሶማሌ ክልል

በሶማሌ ክልል አስር ወረዳዎች እና ሁለት ከተሞች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 38 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች አስፈላጊው መድሀኒት ፣ ባለሞያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች መላካቸውን እና በመንግስት ተቋማት እና በግብረ ሰናይ ድርጅቶች የወረርሽኙን ጉዳት ለመቀነስ የሚረዳ ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል።
12/6/20234 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል ድርቅ ያስከተለዉ ቀዉስ

በአማራ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ እየተፈጠረ እንደሆነ በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች ተናገሩ። የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በሰሜን ጎንደር ዞን 3 ወረዳዎች ባደረገው ጥናት ሰዎችና እንስሳት መሞታቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል። በዞኑ 6 ወረዳዎች ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱም ተመልክቷል።
12/6/20234 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

12/4/202320 minutes, 31 seconds
Episode Artwork

የዐርብ፤ ኅዳር 21 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ-ዜና

12/1/202318 minutes, 25 seconds
Episode Artwork

የሐሙስ፤ ኅዳር 20 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽሄት

11/30/202324 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

11/29/202317 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 18 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

11/28/202321 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

በሶማሌ ክልል ስለደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቁ ከመሳይ ጋ የተደረገው ሙሉ የቀጥታ መስመር ቃለ መጠይቅ

11/28/20237 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

የከፋ ረሃብ አደጋ በትግራይ

በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ ብቻ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸው ተገለፀ። በወረዳው ካለፈው ዓመት ወዲህ ዝናብ ባለመዝነቡና በሌሎች ምክንያቶች ከፍተኛ ረሃብ ተከስቷል። ባሉት 5 ወራት ብቻ በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ ሌሎች ከ95 ሺህ በላይ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸው ገልጿል።
11/27/20234 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

ሱዳን በወረራ የያዘችው የኢትዮጵያ መሬት ጉዳይ

መንግሥት ሱዳን በሰሜን ጦርነት ወቅት በወረራ የያዘችውን የኢትዮጵያ መሬት በድርድር ለማስመለስ የሱዳንን ከጦርነት መውጣት እና ሰላም መሆን እየጠበቀ መሆኑን ማስታወቁ "ሱዳን ሰላም የሚሆነው መቼ ነው" የሚለውን ጥያቄ እርግጠኛ ሆኖ መመለስ ስለማይቻል የቀረበው ምክንያት ከመርህ አንፃር አሳማኝ አለመሆኑ ተገለፀ።
11/27/20234 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

ከሰላም ስምምነቱ መደናቀፍ በኋላ የቀጠለው የኦሮሚያ ግጭት

በኢትዮጵያ መንግስት እና (ኦነግ-ኦነሰ) ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛንያ ዳረሰላም ሲካሄድ የቆየው የሰላም ስምምነት መክሸፉን ተከትሎ በኦሮሚያ የሚታየዉ ግጭት መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ነዋሪዎች እንዳሉት ተስፋ የተጣለበት የሰላም ድርድር ከተደናቀፈ ወዲህ ግጭት አለመረጋጋቱ ቀጥሏል፡፡
11/27/20234 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

አስቸኳይ ድጋፍ የሚሹት የዳሰነች ተፈናቃዮች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ሙላት የተፈናቀሉ ከ79 ሺህ በላይ ነዋሪዎች “ የዕለት ደራሽ የምግብ ድጋፍ ባለማግኘታችን ተቸገርን “ አሉ ፡፡ ነዋሪዎቹ በጎርፍ ሙላት ከተፈናቀሉ ከአንድ ወር በላይ ቢያስቆጥሩም አስከአሁን የምግብ ድጋፍ ባለማግኘታቸው ለረሀብ መዳረጋቸውን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
11/27/20233 minutes, 40 seconds
Episode Artwork

የዐርብ፤ ኅዳር 14 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

11/24/202319 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

በኢትዮጵያ አህዮችን ከጥፋት የማዳን ጥሪ

በኢትዮጵያ የአህያ እርድና ግብይት ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ህክምና ባለሞያው ዶክተር ዘላለም ኃይሉ ለዶይቸ ቬለ እንደገለጹት፦ ድርጊቱ የኅብረተሰቡን ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እሴቶች የሚያናጋ ከመሆኑም ባሻገር፤ የገጠሩን ነዋሪ የኢኮኖሚ መሠረት የሚያናጋ ነው።
11/24/20233 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የሕዳር 13 ቀን 2016 ዜና መጽሔት

11/23/202321 minutes, 16 seconds
Episode Artwork

የረቡዕ፤ ኅዳር 12 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ-ዜና

11/22/202319 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

የህዳር 10 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መጽሔት

11/20/202318 minutes, 55 seconds
Episode Artwork

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ጀርመንን ለመጎብኘት በርሊን ገቡ

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬጄፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጀርመንን ለመጎብኘት መዲና በርሊን ገቡ። የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት በጦርነቱ ያላቸዉ አቋም ከቱርኩ ፕሬዚደንት የተለየ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ወደ በርሊን የመጡት ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ጉዳዮች ከመራሔ መንግሥቱ ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
11/17/20234 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

የፓስፓርት ለማግኘት እና ለማደስ ያለ ችግር በኢትዮጵያ

አዲስ ለማግኘትም ይሁን ነባር ፓስፓርት ለማደስ አመልክተው ለረጅም ጊዜ ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ወደ 200 ሺህ የሚደርሱ አመልካቾች እስከ ታህሣስ መጨረሻ ፓስፖርት እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረት ላይ መሆኑን የኢሚግሬሽን አስታወቀ። ይሁን እና ከፓስፓርት እድሳትና አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በሌብነትና ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ ሕዝብን አማረዉታል።
11/17/20234 minutes, 12 seconds
Episode Artwork

በፌዴራል ስርዓቱና ህገመንግስቱ ላይ የተደረገ ዳሰሳዊ ጥናት

በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት እና ህገመንግስት ላይ ያተኮረው ጥናት ይፋ ሆነ፡፡ አፍሮባሮሜትር የተሰኘው የጥናት ተቋም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስርዓት እና ህገመንግስት ጉዳይ ላይ ያስጠናውን የትናት ውጤት ነው ዛሬ ይፋ ያደረገው፡፡
11/17/20234 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ግሎባል አሊያንስ በድርቅ ለተጎዱ ዕርዳታ እያሰባሰበ ነው

ግሎባል አሊያንስ በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ መሆኑን አስታወቀ። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከተመሰረተበት ካለፉት አስር ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ችግር ሲከሰት ፈጥኖ እየደረሰ ሲሆን አሁንም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው።
11/17/20234 minutes, 8 seconds
Episode Artwork

በኢትዮጵያ እያሻቀበ የመጣው የስደተኞች ቁጥርና አሳሳቢ ይዞታው

በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች የሚያስፈልጓቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት እንቅፋት የሆኑ ችግሮች መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ምዝገባ መቆሙን እና የስደተኝነት ሁኔታ አወሳሰን እየተሰራ አለመሆኑን የስደተኞች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ፍልሰተኞች መብት የሥራ ክፍል ኃላፊ እንጉዳይ መስቀሌ ተናግረዋል
11/16/20234 minutes, 25 seconds
Episode Artwork

የሕዳር 06 ቀን 2016 ዜና መጽሔት

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በደረሰው የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 28 አሻቅቧል። የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ከሣምንት በፊት በተፈጸመ ጥቃት ከ3 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት ያሰጋቸው የሲቪክ ማኅበራት ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ደብዳቤ ጽፈዋል። እነዚህን ጨምሮ ስድስት ዘገባዎች በዛሬው የዜና መጽሔት ይቀርባሉ።
11/16/202325 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም.

11/15/202320 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የሕዳር 4፣2016 ዜና መፅሔት

11/14/202318 minutes, 40 seconds
Episode Artwork

በመቐለ ከተማ ማረምያ ቤት የቀጠለዉ ኹከት እና ግድያ

በመቐለ እስርቤት ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 4 እስረኞች ሞቱ። የእስርቤቱ ሐላፊዎች እስረኞች ለማምለጥ ሲሞክሩ እርምጃ መወሰዱን አምነዋል። በእስርቤቱ ውስጥ ሁከቱ የተፈጠረው ካለፈው ቅዳሜ ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ነዉ፤ ሌሎች 9 መቁሰላቸውን የመቐለ ማረሚያ ቤት አስተባባሪ ኮማንደር አማኑኤል ፍስሃ ገለፁ።
11/13/20233 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

እልባት የሚሹት የእገታ ወንጀሎች ነዋሪዉን እያማረሩ መሆኑ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን እየተባባሰ የመጣዉ የእገታ ወንጀል እንዳማረራቸው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በአርሲ ዞን ሰዎችን አግቶ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብን የመጠየቅ ህብረተሰቡን አማሯል ብለዋል፡፡ የዞኑ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩ አልፎ አልፎ በደናማ አከባቢዎች መሰል ተግባር ቢታይም፤ የመኪና መንገድ እና ከተሞች ዙሪያ ይህ ተግባር አይሰማም ብሏል።
11/13/20234 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ሀገራዊ አንድነት እና ፈተናው

የፌደሬሽን ምክር ቤት በየዓመቱ የሚያከብረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የበዓሉ አክባሪዎች "ለረጅም ዘመናት ይዘውት የቆዩትን አብሮነት እንዲያፀኑ ፣ ከልዩነት ይልቅ አንድነትን እንዲያጎለብቱ አግዟል" ሲሉ የምክር ቤቱ ዛሬ ተናገሩል። ይህ ምን ያህል ተጨባጭ እውነታ ነው ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ለጋዜጠኞች እድል በመነፈጉ ምላሻቸው ሊካተት አልቻለም።
11/13/20234 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

11/8/202319 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 27፣2016 ዜና መፅሔት

11/7/202318 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም.

11/6/202320 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

መንግሥት በአማራ ክልል አለመረጋጋት ከስጋት ደረጃ ወርዷል ማለቱ

የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ዕዝ ስለክልሉ አሁናዊ ይዞታ መገምገሙን አንስተው ትናንት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፤ ለመፍረስ ተቃርቦ የነበረውን ክልል ከመፍረስ መታደግ ተችሏል ብለዋል፡፡
11/3/20234 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

በኢትዮጵያ ሐቀኛ የሽግግር ፍትሕ እንዲሰፍን አሜሪካ ጥሪ ማቅረቧ

በኢትዮጵያ ተበዳዮችን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ ስርዓት እንዲሰፍን ዩናይትድስቴትስ ጥሪ አቀረበች። ብሊንከን፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት ያስቆመው የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመት በማስመልከት ባወጡት መግለጫ፤ በዐማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ለማስቆም በአስቸኳይ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።
11/3/20234 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

የፕሪቶርያ ስምምነት አፈፃፀም አንደኛ ዓመት እና የመቐለ ነዋሪዎች አስተያየት

የሁለት ዓመቱ ደም አፋሳሽ ጦርነት ያስቆመ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ሞልቶታል። ይህ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል የተደረገ ውል ጦርነት ከማስቆም በዘለለ በርካታ በአወንታ የሚታዩ እርምጃዎች የፈጠረ ነዉ። የመቐለ ነዋሪዎች ምን አስተያየት አላቸዉ?
11/3/20233 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

በጋምቤላ ከባድ ዝናብ ያስከተለዉ ጎርፍ አስርሽዎችን አፈናቀለ

በጋምቤላ ክልል በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም በባሮ፣ጊሎና አኮቦ ወንዝ ሙላት ባስከተው አደጋ ከ36ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ቢሮ አመልክተዋል፡፡ በጋምቤላ ከተማ አራት ከሚደርሱ ቀበሌዎች ውስጥ በወንዝ ሙላት ተፈናቅለው የነበሩ 6ሺ የሚሆኑ ዜጎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተመልክቷል።
11/3/20233 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ስምምነት 1ኛ ዓመት፣ ልዩ ዝግጅት

11/2/202327 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

የትግራይ ተፈናቃዮች ቅሬታ

የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭት የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ አንድ ዓመት ቢደፍኑም በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ክልል የተፈናቃሉ ነዋሪዎች ወደየቀያቸዉ አለመመለሳቸዉ እንዳሳሰባቸዉ እየተናገሩ ነዉ። የተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ስምምነቱ ሲፈረም ወደየቀያችን እንመለሳል የሚል ተስፋ አሳድረን ነበር።
11/2/20233 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

የፕሪቶሪያው ስምምነት አንደና ዓመት እና የህዝብ አስተያየት

ከተፈረመ ዛሬ ድፍን አንድ ዓመት የሞላው ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ኃይሎች እና በኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች መካከል ይደረግ የነበረውን ጦርነት ያበቃው ስምምነት በብዙ መልኩ በህዝብ ይነሳል፡፡ ስምምነቱ በአከባቢው ደም አፋሳሹን ጦርነት በመግታት ረገድ ያበረከተውን አስታዋጽኦ አጉልተው የሚያነሱ በርካቶች ናቸው፡፡
11/2/20233 minutes, 31 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

11/1/202317 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

የማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ-ዜና

10/31/202318 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

10/30/202317 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል ንፁሃን በድሮን ድብደባ ተገድለዋል - ኢሰመኮ

በአማራ ክልል ለወራት በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት ድሮንን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። በደብረ ማርቆስ በደምበጫ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ የአንድ ዓመት ከሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪሎች ተገድለዋል።
10/30/20234 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ በስብዓዊ መብት ቀውስ ላይ ነች መባሉ

የፕሮፊሰር መስፍን ወልደ ማሪያም መታሰቢያ ፈውንዴሽን ባዘጋጀው ጉባዔ «ኢትዮጵያ በስብዓዊ መብት ቀውስ ላይ ነው ያለችው» ተባለ። በጉባኤዉ የፖለቲካ ችግርና ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በሰላምና በንግግር ለመፍታት አቅምና ሞራል ያጡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ችግር አሁንም በየአካባቢው ጦርነት እየተካሄደ ሰው እየሞተና ህዝቦች እየተቸገሩ ነዉ።
10/30/20233 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

የዓርብ ጥቅምት 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽሄት

10/27/202317 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም.

10/26/202323 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የረቡዕ ጥቅምት 14 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

10/25/202318 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

ወደ ጋምቤላ የሚሰደዱ ደቡብ ሱዳናዉያን ቁጥር እየጨመረ ነዉ ተባለ

ከደቡብ ሱዳን ግጭት በመሸሽ ወደ 9ሺ የሚጠጉ ሰዎች ወደ ጋምቤላ ክልል መሻገራቸውን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ስደተኞቹ በጋምቤላ ክልል ፒኝዶ በተባለ ቦታ ተጠልለው እንደሚገኙ አገልግሎቱ አስታዉቋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚሻገሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጸዋል፡፡
10/24/20233 minutes, 12 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 12 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

10/23/202318 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

ለጦርነቱ ውጤት የዓረና ወቀሳ

10/21/20233 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

አፈናቃዮችን ማን ተጠያቂ ያድርግ?

10/21/20233 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

ፀረ-ሴማዊነት በጀርመን ተቀባይነት የለዉም፤ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ ነዉ

10/20/20235 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

የሐሙስ፤ ጥቅምት 8 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽሄት

10/19/202326 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

አዲሱ «አዲስ ፓሪስ መጽሔት»

«አዲስ ፓሪስ» ማለት በአዲስ አበባ እና በፓሪስ ከተሞች ያሉትን የባህል የፍልስፍና፤ የታሪክ እና የቱሪዝም ለየከተሞቹ የሚያስተዉቅ መሳርያ ነዉ። ፓሪስ የሚገኘዉን ለአዲስ አበባ፤ አዲስ አበባ የሚገኘዉን መረጃ ፤ ለፓሪስ ከተማ ማለት ነዉ። ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዝ የፈረንሳይ አገር ጎብኝ «አዲስ ፓሪስ»ን ከያዘ ብዙ ነገሮችን የማግኘት እድል ይኖረዋል።
10/19/202313 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 7፣ 2016 ዜና መፅሔት

10/18/202318 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. ዜና መጽሄት

10/17/202318 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መፅሔት

10/16/202318 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

በትግራይ የ3 ቀናት ክልላዊ ሃዘን ታወጀ

10/14/20233 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

የሃይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪ

10/14/20234 minutes, 6 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም.

10/13/202317 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ/ም የዜና መፅሔት

10/12/202327 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

በሃማስ ጥቃት በርካታ ቤተ እስራኤላዉያን ተገድለዋል ተባለ

በተለያዩ ሃገራት «አሸባሪ ድርጅት» ተብሎ የተፈረጀዉ በፍልስጤሙ ሐማስ የተገደሉ እስራኤላዉያን ቁጥር ከ1,200 በላይ መድረሱ እየተዘገበ ነዉ። የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥን በቦምብና ሚሳዬል መደብደቡን ዛሬም ለ 6 ኛ ቀን ቀጥሏል። ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግ የሚጠይቀዉ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲከበር እያሳሰቡ ነዉ።
10/12/20234 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 30፣2016 ዜና መፅሔት

10/11/202319 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

10/10/202325 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም.

10/9/202319 minutes, 43 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 25 ቀን 2016 ዜና መፅሔት

10/6/202321 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ረቡዕ መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም.

10/4/202319 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 22 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

10/3/202319 minutes, 11 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 21 ቀን 2016 የዜና መጽሔት

10/2/202313 minutes, 55 seconds
Episode Artwork

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪና የኑሮ ውድነት

9/30/20233 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 17፣2016 ዜና መፅሔት

9/28/202323 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

የረቡዕ መስከረም 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

9/27/202315 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 15፣2016 ዜና መፅሔት

9/26/202322 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፤ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ

9/25/202315 minutes, 15 seconds
Episode Artwork

የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ ያደረጉት የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ውጤት አልባ ሆኖ ስለመጠናቀቁ በግብጽ በኩል ተገለፀ። መንግሥት እስካሁን በግልጽ ያለው ነገር ባይኖርም የግድቡ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ «ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሔ ላይ ለመድረስ በበጎ መንፈስ ትሠራለች» ሲሉ ጽፈዋል።
9/25/20234 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

በትግራይ የሕግ የበላይነት እንዴት ይረጋገጥ ይሆን?

በትግራይ ተፈፀመ ለተባለ የእርዳታ ማጭበርበር እና ሌሎች ዝርፍያዎች የሕግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ። በክልሉ የመንግስት የሲቪል ባለስልጣናት እንዲሁም ወታደራዊ አመራሮች በዝርፍያ መዘፈቃቸውም እየተገለፀ ነዉ። የሕግ ምሁራን በበኩላቸዉ ለዚህ ተጠያቂነት ማስፈን ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።
9/25/20234 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

የጎንደር ከተማ ወቅታዊ ሁኔታና የከተማዋ የአስቸኳ ጊዜ እዝ መግለጫ

ፋኖ በጎንደር ከተማ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመክፈት ያደረገውን ሙከራ “አከሸፍኩ” ሲል የጎንደር ከተማ የአስቸኳ ጊዜ እዝ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ ነዋሪዎች ዛሬ አልፎ አልፎ ተኩስ ቢሰማም የማህበራዊ አገልግሎቶች በከተማዋ ባይኖሩም መጠነኛ መረጋጋት እንዳለ ተናግረዋል፡፡
9/25/20233 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፤ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም

9/22/202323 minutes, 8 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 10፤2016 ዜና መፅሔት

9/21/202323 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት

9/20/202318 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም

9/20/202319 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

በጦርነቱ የሞቱ የትግራይ ኃይሎች መርዶ ይነገራል መባሉ

በጦርነቱ ወቅት የሞቱ የቀድሞ የትግራይ ኃይል ለቤተሰቦቻቸው መርዶ የመንገር ስርዓት በቅርቡ በይፋ እንደሚካሄድ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩ በትክክል ባያስቀምጡትም «በሺዎች የሚቆጠሩ» ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸው ተናግረዋል።
9/20/20234 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የዓይን እማኞች አስተያየት

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ዛሬም ውጊያዎች እንዳሉነዋሪዎች እየተናገሩ ነው፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራጎዳና በተባለች ከተማ ባለፈው እሁድ በተቀሰቀሰ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ከአካባቢዉ አመለጥን ያሉ ሰዎች ከዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
9/19/20233 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

በሕገወጥ ስደተኞች የተጨናነቀችዉ ጣልያን እና የአዉሮጳ ህብረት የመፍትሄ ሃሳብ

ጣሊያን ዛሬም እንደገና በስደተኖች እይተጥለቀለኩ ስትል ጩኸት እያሰማች ነው። ካለፈው የጥር ወር ወዲህ በሜዲትራኒያን ባሕር በኩል ወደ ጣሊያን የገቡ ስደተኖች ቁጥር 126 ሺ ደርሷል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በ24 ሰአት ውስጥ ከሰባት ሺ በላይ ስደተኖች በጣልያንዋ ላምፔዱዛ ደሴት መግባታቸው ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒንን አስደንግጧል።
9/19/20234 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት ፦ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም.

9/18/202333 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሰላም የራቃቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች ነዋሪዎች ስጋት

አርሶ አደሩ የዛሬ ሶስት ዓመታት ገደማ በአከባቢያቸው የከፋው የታጣቂዎች እንቅስቃሴና የፖለቲካ መዘበራረቅ ከሚወዱትና መተዳደሪያቸው ከሆነው ቀዬያቸው እንዳስወጣቸውና ለእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ እንዳስገደዳቸውም ጠቁመዋል።አርሶ አደሩ አሁን የናቀፈቀን ከምኑም በላይ ሰላም ነው ባይም ናቸው፡፡«ከከተማ አንድ እርምጃ ወጥተን ማረስ አይታሰብም ብለዋል።
9/18/20234 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 4 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽሄት

9/15/202318 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 4 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሙሉ ሥርጭት

9/15/20231 hour
Episode Artwork

የመስከረም 3፣2016 ዜና መፅሔት

9/14/202322 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

ከስልጤ ዞን የተፈናቃሉ ነዋሪዎች የርዳታ ጥሪ

በሥልጤ ዞን ቅበት ከተማ መፈናቀሉ ሊከሰት የቻለው በከተማው መተት ተደረጎባቸዋል የተባሉ ሴቶችን ለመፈወስ በሚል ወጣቶች ባደረጉት እንቅስቃሴ መሆኑን ተፈናቃዮቹ ተናግረዋል ፡፡ ፈውሱን ለማካሄድ በሚል በከተማው የመግቢያና መውጫ ሥፍራዎች ላይ ቁራን ለማሰማት የሞከሩ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን የጠቀሱት ተፈናቃዮቹ
9/14/20233 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

ስርቆት፣ ዘረፋ፣ እገታና ሥርዓተ አልበኝነት በትግራይ

በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች፥ በተለይም በሴቶች ላይ የሚደርስ የጥቃት እና ግድያ ዜና መስማት የተለመደ ሲሆን አብዛኞቹ ለቀናት ከሚቆይ የማሕበራዊ ሚድያ ዘመቻ ውጭ ፍትህ የማረጋገጥ ተግባራትም በስፋት አይስተዋሉም
9/14/20233 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

የታሰሩ ተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት ይዞታ

በአማራ ዋና ዋና ከተሞች ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ሸዋ ሮቢት እንዲሁም በአፋር አዋሽ አርባ የሚገኙ ናቸው በተባሉት ማቆያ ስፍራዎች ተይዘዉ ይገኛሉ የተባሉት ተጠርጣሪዎች 764 ናቸው ሲል ለመጀመርያ ጊዜ ትናንት መግለጫ የሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን አፈፃፀም እንዲመረምር የተዋቀረው መርማሪ ቦርድ አስታውቋል።
9/14/20233 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 1 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ልዩ መሰናዶ

9/12/202342 minutes, 31 seconds
Episode Artwork

የአማራዉ ክልል ቀዉስ ጥላ ያጠላበት የ 2016 ዘመን መለወጫ

በኢትዮጵያውያን ዘንድ በድምቀት የሚከበረዉ የዘመን መለወጫ ዋዜማ በአማራ ክልል ቀዝቃዛ እንደሆነ ተመለከተ። በክልሉ በሚታየዉ የሰላም እጦት ምንክንያት የአዲስ ዓመት አቀባበል እና አከባበሩ ላይ ጥላ እንደጣለበት በደብረማርቆስ፣ በደብረታቦር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ፣ በፈረስ ቤት፣ በለሚ፣ በደሴና በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ገለፁ።
9/11/20234 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ጳጉሜ 6 ቀን 2015 ዓ.ም

9/11/202318 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

በድሬደዋ እና ሐረር በአዲስ ዘመን መለወጫ የታየዉ የዋጋ ንረት

በድሬደዋ እና ሀረር ከተሞች የአዲስ አመት በዓል ገበያ በዶሮ እና ፍየል ዋጋ ላይ ጭማሪ ማሳየቱን ሸማቾች እና ሻጮች ተናግረዋል። በሀገሪቱ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት በተለያዩ ምርቶች ላይ ያስከተለው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በተለይ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኘውን ህብረተሰብ ክፉኛ እየፈተነ መሆኑንም አስተያየታቸውን የሰጡ የድሬደዋ ነዋሪዎች ተገልፀዋል።
9/11/20234 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

ከመቐለው ስልፍ ጋር በተገናኘ የታሰሩ የተቃዋሚፓርቲ አመራሮች ከእስር መለቀቃቸዉ

ከመቐለው ሰልፍ ጋር በተገናኘ ታስረው ፍርድቤት እንዲፈተቱ የወሰነባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፥ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሦስት ቀናት በኃላ ለቀናት ዛሬ ማምሻው ተለቀቁ። በሰልፉ እና ከሰልፉ በኃላ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈፀሙ ተገልጿል።
9/11/20233 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተጠናቋል መባሉ እና አንደምታዉ

ኢትዮጵያ በግዙፉ አባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛው ዙር የዉኃ ሙሌት መጠናቀቅ በትናንትናው እለት ተገልጿል፡፡ ይህ የተገለጸው ረዘም ላለ ጊዜ በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሚያደርጉት የሦስትዮሽ ድርድር ተቋርጦ ከቀጠለ ከጢቂት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ ግብጽ ጉዳዩ ስምምነቱን ይጥሳል ብላለች።
9/11/20234 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

የጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

9/8/202317 minutes, 40 seconds
Episode Artwork

ዜና መፅሔት፣ ጳጉሜ 2፣2015

9/7/202324 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

የረቡዕ ጳጉሜ 1 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ዜና መጽሄት

9/6/202317 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ/ም የዜና መጽሔት

9/5/202320 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

9/4/202320 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ/ም የዜና መጽሔት

9/4/202321 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም.

9/1/202329 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

8/30/202321 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

አረና ትግራይ የፕሪቶሪያ ስምምነት በአስቸኳይ ይተግበር አለ

ትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲኖራት እንደሚታገል ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ዐስታወቀ። ዓረና ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፦ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥትን በማሻሻል አዲስ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ውል ለመመስረት ከሌሎች በኢትዮጵያ ካሉ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር በጋራ እንደሚሠራ ገልጿል።
8/29/20233 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. መጽሄተ ዜና

8/29/202319 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

8/28/202314 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፦ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም.

8/25/202318 minutes, 46 seconds
Episode Artwork

የአሸንዳ በዓል አከባበር በመቀሌ

ከ2011 ዓመተምህረት በኃላ በተለያዩ ምክንያቶች የቀድሞ ድምቀቱ አጥቶ እና ሲስተጓገል የቆየው በትግራይ ሴቶች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረው የአሸንዳ በዓል ከአራት ዓመታት በኃላ ዘንድሮ በድምቀት እየተከበረ ነው
8/22/20233 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

ኪራሙ ወረዳ ሰዎች ተገደሉ፣ ከብቶች ተዘረፉ

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ ባደረሱት ጥቃት 6 ሰዎች ገደሉ፤ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል። የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንዳሉት ታጣቂዎቹ በሁለት ቀበሌዎች ላይ ዘምተዉ ሰዉ ከመግደልና ንብረት ከማጥፋታቸዉ በተጨማሪ የቁም እንስሳትንም ዘርፈዋል፡፡
8/22/20233 minutes
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ሰኞ

8/21/202313 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በተቃዋሚዎቻቸው አንደበት

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ፤ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው በይፋ ከተገለጸ 11 ዓመት ሊሞላው በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተዋል። መለስ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በስልጣን በነበሩባቸው ዓመታት በሀገሪቱ በነበራቸው የመሪነት ሚና ላይ ደጋፊዎቻቸውም ሆኑ ተቃዋሚዎቻቸው በተለያየ መንገድ ይገልጿቸዋል።
8/20/20234 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

ኒዠር የዓለም ኃያላን የእጅ አዙር መፋለሚያ

​​​​​​​የኒዠር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙምን ከሦስት ሳምንት በፊት በኃይል ከሥልጣን አዉርዶ መንበረ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊ ኹንታ ለምዕራባውያን በተለይ ለፈረንሳይ ሙሉ ለሙሉ ጀርባውን ሰጥቷል ። በአንጻሩ ከምዕራባውያን ጋር በዩክሬን ጉዳይ የምትወዛገበው ሩስያ ለወታደራዊ ኹንታው ድጋፏን ዐሳይታለች ። ፍጥጫው ወዴት ያመራ ይሆን?
8/19/20235 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

ብሪክስ፦ የሩስያው ፕሬዚደንት ጉዳይ አወዛግቧል

8/19/20233 minutes, 40 seconds
Episode Artwork

ኤኮዋስ በኒዤር ጉዳይ ከማስጠንቀቂያ አልዘለለም

8/19/20235 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

8/18/202318 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የወባ እና የደንጊ በሽታዎች ወረርሽኝ ስጋት በድሬዳዋ

ነዋሪዎች በአብዛኛው በችኩንጉንያ እንደታመሙ ቢገልፁም ኃላፊዋ በተለይ ወደ መንግስት ህክምና ተቋማት ከመጡ ሰዎች ተወስዶ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መሰረት ምንም የችኩንጉንያ በሽታ ውጤት እንዳልተገኘ አስረድተዋል።አሁን ያለው የአየር ንብረት ሁኔታ ተደምሮ የወረርሽኙ መጠን እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣዩ ጊዜ ስጋት መሆኑን ተናገረዋል።
8/17/20234 minutes, 1 second
Episode Artwork

የነሐሴ 11 ቀን፣ 2015 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

8/17/202326 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

እስራኤል የቤተ እስራኤላውያንን የፍልሰተኞችን ፖሊሲ ልታሻሽል ነው

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ እስራኤል ቤተእስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ፖሊሲዋን ልትከልስ እንደምትችል የሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ሚኒስቴር ዐስታውቋል። የእስራኤል መንግስት ውሳኔ የተሰማው ከአማራ ክልል ተጨማሪ ቤተእስራኤላውያንን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌለ ማሳወቁን ተከትሎ ቤተእስራኤላውያን ለተቃውሞ አዳበባይ ከወጡ በኋላ ነው።
8/17/20234 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

«የትግራይ ነፃነት ፓርቲ» በህወሓት ላይ ያቀረበው ክስ

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ ገብረስላሴ ካሕሳይ« ህዝባችን በችግር ላይ ችግር እየተደራረበበት የሞት ሞት እየሞተ ነው። የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንኳን በህወሓት ካድሬዎች ተፈርፎ የሚበላው አጥቷል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ከተቋቋመ በኃላ እንኳን በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በረሀብ እና በሽታ እንደቅጠል እየረገፉ ነው" ብለዋል።
8/17/20233 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

8/16/202318 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 9 ቀን፣ 2015 ዓ.ም መጽሄተ ዜና

8/15/202318 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሕዝብ አስተያየት

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ወቅታዊ የፀጥታ መደፍረስን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት በትናትናው ዕለት አደጋውን ለመቀልበስ ይረዳኛል ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸድቋል ።
8/15/20234 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

የምዕራብ ወለጋ ተፈናቃዮች ተማጽኖ

ከተለያዩ ስፍራዎች ተፈናቅለው በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ የሚገኙ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ለአራት ወራት ያህል ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ፡፡ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከሶስት ወራት በፊት የቀረበው ድጋፍ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ መዳረሱን ገልጸዋል፡፡ በየወሩ ሰብአዊ ድጋፍ ይመጣል ቢባልም ለወራት ድጋፍ እንደላገኙ ጠቁሟል፡
8/15/20233 minutes, 34 seconds
Episode Artwork

የዶናልድ ትራምፕ 4ኛ ክስ ምን ለየት ያደርገዋል?

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራም ላይ በዚህ ዓመት አራተኛው ክስ ዛሬ ማለዳ ቀርቦባቸዋል ። ክሱም በጆርጂያ የምርጫ ውጤትን ለማስቀየር በመሞከር በሚል ነው ክሱ የቀረበባቸው ። ፕሬዚዳንቱ እና ደጋፊዎቻቸው ክሱን በማጣጣል ለቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የገንዘብ እና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻቸውን ቀጥለዋል ።
8/15/20233 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ጠንካራ ሙግት የተስተናገደበት የምክር ቤት ዉሎ

የሕዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ላይ ትናንት የተወያየው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ ጠንካራ ውይይት እና የሀሳብ ፍጭት አስተናግዷል።
8/15/20234 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ዛሬ አጸደቀ። አዋጁን 16 የፓርላማ አባላት ሲቃወሙት፤ 12 አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። በአማራ ክልልና "እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች" ተግባራዊ እየተደረገ ለሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ተሰይሟል።
8/14/20235 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

"ወደ ያልታወቀ ሥፍራ ሲወስዷቸው አይቻለሁ"

"በየ ክፍሉ ሰማንያ አምስት ፣ ሰማንያ አምስት ሰው አንድ አንድ ክፍል አድርገው አስገቡን። ከዚያ ሌሊት ላይ ጫኑን። አሁን እኛ አካባቢ አብዛኛው የአቃቂ እና የቱሉ ዲምቱ አካባቢ ሰው ነው የታሰረው"
8/14/20232 minutes, 46 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም.

8/11/202316 minutes, 17 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

8/10/202323 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም.

8/9/202319 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

የአማራ ክልል እንዴት ዋለ?

በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች እንደሰሞኑ ሁሉ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ማደሩን እና መዋሉ እየተነገረ ነዉ። የአማራ ክልል መዲና በሆነችዉ ባህርዳር ለሊቱን እስከ ዛሬ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ኩስ ሲሰሰማ እንደነበር እና በተለይ በከተማዋ በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ከፍተኛ ተኩስ እንደነበር ተነገረ።
8/8/20234 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ አመራሮች ውዝግብ

ስምምነቱ በሰላም እና ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ መሆኑም ተገልጸዋል፡፡ ሆኖም የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤ.ህ.ነ.ን.) የፓርቲውን ሊቀ መንበር ከኃላፊነት ማንሳቱን ገልጸዋል፡፡ ሊቀመንበሩ ከፓርቲው የታገዱት ሐምሌ ፓርቲው ያልተነጋገረበትና ያላጸደቀውን ስምምነት ከክልሉ መንግስት ጋር ተፈራርመዋል በሚል ነው፡፡
8/8/20234 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ,ም ማክሰኞ

8/8/202319 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም የዜና መጽሔት

8/7/202319 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ሐምሌ 28 ቀን 2015

8/4/202319 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

ግጭትና የመከላከያ ማስጠንቀቂያ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚደረገዉ ግጭት፣ የሚፈፀመዉ ጥቃትና የሚጣለዉ አደጋ አሁንም አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።አራት ዓመት የዘለቀዉ ግጭትና ጥቃት በርካታ ሕዝብ አፈናቅሏል።ገበሬዉ እንዳያርስ ከስፍራ ስራ እንዳይንቀሳቀስም እንቅፋት ሆኖበታል።
8/3/20233 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የኒዠር መፈንቅለ መንግስትና ማስጠንቀቂያዉ

ማስጠነቀቂያና ዛቻዉ ግን የወለፊንድ ባርቆ ለኒዠር ወታደራዊ ሁንታ ድጋፍ እያስገኘለት ነዉ።ማዕቀብና ማስጠንቀቂይው ግን በመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎቹ ላይ ተጽኖ የፈጠረ አይመስልም
8/3/20233 minutes, 46 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም.

8/2/202319 minutes, 9 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ማክሰኞ

8/1/202317 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

በኢትዮጵያ አዲሱ የአሜሪካ አምባሳደር እና አቋሟቸዉ

አዲሱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኧርቪን ሆሴ ማሲንጋ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር በርካታ ስራወች መሰራት እንዳለባቸው ገለጹ። እየተባባሰ የሄደው አለመረጋጋትና በብሄር ላይ የተመሰረተው የእርስ በርስ ግጭት ሃገሪቷን ወደባሰ ቀውስ ውስጥ እየከተታት እንደሆነ ተናግረዋል።
8/1/20234 minutes, 46 seconds
Episode Artwork

በመስቃን እና በማረቆ ማህበረሰብ መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት

በጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ በመስቃንና በማረቆ ማህበረሰብ አባላት መካከል ግጭት መቀስቀሱን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀቀዉ“ያልታወቁ“ የተባሉ ታጣቂዎች አምስት ሰዎችን መገደላቸውንና ሌሎች ስምንት ማቁሰላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰሜን ዲዳ በተባለ ቀበሌ አንዳቸው የሌላኛቸውን ቤቶች ማቃጠላቸውንና የቤት እንስሳትም መዘራረፋቸው ተመልክቷል።
7/31/20233 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓም ሰኞ

7/31/202319 minutes, 25 seconds
Episode Artwork

የህገ-ወጥ አዘዋዋሪ ሰለቦች መብት ጉዳይ

በሰው የመነገድ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ። በሰው መነገድ ወንጀል ተሳታፊዎች ማታለል ደርሶባቸው ከሀገር ከወጡ በኋላ ተጎጂ ዜጎች ለሞት፣ ለአካል ጉዳት ለብዝበዛና ለሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ መገንዘቡን አመልክቷል።
7/31/20233 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

የሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ,ም የዜና መጽሔት

7/28/202315 minutes, 9 seconds
Episode Artwork

ዜና መፅሔት፣ ሐምሌ 20፣2015

7/27/202326 minutes, 46 seconds
Episode Artwork

ዜና መጽሔት፦ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም.

7/26/202321 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

ዜና መፅሔት፣ ሐምሌ 18፣ 2015

7/25/202318 minutes, 31 seconds