Winamp Logo
ስፖርት | Deutsche Welle Cover
ስፖርት | Deutsche Welle Profile

ስፖርት | Deutsche Welle

Amharic, Sports, 1 season, 88 episodes, 14 hours, 43 minutes
About
ት እንቅስቃሴ የሚታይበት ዝግጅት ነው።
Episode Artwork

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ድል ቀንቷዋል፤ የአፍሪካ ዋንጫም ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ ነው

ከአትሌቲክስ ፤ አሜሪካ ቦስተን በተካሄደ የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጉዳፍ ጸጋይ አሸናፊ መሆናቸው፤ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም የደቡብ አፍሪካ አቻውን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸንፏል።
2/5/202410 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

የጥር 20 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች አስደማሚ በሆነ መልኩ ቀጥለዋል ። በ10 ተጨዋቾች የተወሰነው የኤኳቶሪያል ጊኒ በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ለጊኒ እጅ መስጠቱ ብዙዎችን አስቆጭቷል ። ግብጽ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተሸኝታለች ። ውድድሮቹ ቀጥለዋል ።
1/29/20249 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/29/20249 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

የጥር 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት የሚከናወነው የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያዎች ያልተጠበቁ ውጤቶችን እያስተናገደ 3ኛ ዙር ላይ ደርሷል ። በቡንደስሊጋው ባዬርን ሙይንሽን ሽንፈት ሲገጥመው በፕሬሚየር ሊጉ ደግሞ ሊቨርፑል በአስተማማኝ መልኩ ድል አድርጓል ። ኢትዮጵያውያን በአትሌቲክስ ድል ተቀዳጅተዋል ።
1/22/20249 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/22/20249 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

ከአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ-ገብርኤል ጋ የተደረገውን ሙሉ ቃለ መጠይቅ እዚህ ያገኛሉ

1/15/20247 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በዚህ ሳምንት ቅዳሜ ስለሚጀምረው የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል። ኢትዮጵያዊት አትሌት ፈጣን ሰአት ስላስመዘገበችበት የዱባይ የማራቶን ሩጫ እና የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ግጥሚያ ዘገባ ይኖረናል።
1/8/202410 minutes
Episode Artwork

ከስፖርት ጋዜጠኛ ዖምና ታደለ ጋ የተደረገው ሙሉ ቃለ መጠይቅ እዚህ ይገኛል

1/8/20246 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/8/202410 minutes
Episode Artwork

የታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የስፖርት ዝግጅት

1/1/202410 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች

ከአትሌቲክስ መረጃዎች ፤ ኬንያዊቷ አትሌት ቢአትሪክ ቼቤት ትናንት እሁድ ባርሴሎና ውስጥ በተደረገው የ5 ኪ/ሜ የጎዳና ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸነፋለች። ቼቤት በጎርጎርሳውያን አዲስ ዓመት ዋዜማ የራሷ ባደረገችው በዚሁ ክብረ ወሰን የገባችበት ሰዓት 14 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ ሆኖ ተመዝግቧል።
1/1/202410 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 15 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፦ ሊቨርፑልን በሜዳው ነጥብ ያስጣለው ማንቸስተር ዩናይትድ ቅዳሜ ዕለት በዌስትሀም ዩናይትድ የ2 ለ0 ሽንፈት አስተናግዷል ። ማንቸስተር ሲቲ በፊፋ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የብራዚሉ ፍሉሚኔንዜን ዐርብ ዕለት 4 ለ0 አሸንፎ ዋንጫውን ወስዷል ። የአበረታች ንጥረ ነገር ጉዳይ የኢትዮጵያ አትሌትን ሰቅዞ ይዟል ።
12/25/202310 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/25/202310 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

ከስፖርት ጋዜጠኛ ዖምና ታደለ ጋ የተደረገው ሙሉ ቃለ መጠይቅ እዚህ ይገኛል

12/25/20238 minutes, 34 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/18/20239 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የታኅሣስ 1 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከስዊትዘርላንድ እስከ ዩናይትድ ስቴትስ፤ ከቱርክ እስከ ቻይና በትናንትናው ዕለት በርካታ ድሎችን ተቀዳጅተዋል ። በአንጻሩ፦ «የኢትዮጵያ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን» ከፓሪስ ኦሎምፒክ በፊት ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገሮች ላይ ጥብቅ ምርመራ እና ቁጥጥር እንደሚያደርግ ዐስታውቋል ።
12/11/202310 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/11/202310 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ከምስጋናው ጋ የተደረገው ሙሉ ቃለ መጠይቅ እዚህ ይገኛል

12/11/202310 minutes, 6 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 24 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ስፔን ውስጥ ትናንት በቫለንሺያ ማራቶን በወንዶችም በሴቶችም አመርቂ ድል አስመዝግበዋል ። ድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ የጀርመን ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ማንሳት ችሏል ። የኢትዮጵያ ጁዶ ፌፌሬሽን ምሥረታ ውዝግብ አስነስቷል ። የሚመለከታቸውን አናግረናል ።
12/4/202311 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/4/202311 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

11/27/202310 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 17 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የፊታችን እሁድ ስፔን ውስጥ ለሚካሄደው የቫለንሺያ ማራቶን አትሌት ቀነኒሳ እና ዓልማዝ አያና እጅግ ከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል ናቸው ።ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ከሊቨርፑል ጋ ባደረገው ወሳኝ ግጥሚያ ሳያሸነፍ ቀርቷል ። ሁለቱም ነጥብ ተጋርተዋል ። አርሰናል በ1 ነጥብ ልዩነት ብቻ የመሪነቱን ስፍራ ተቆናጧል ። ሙሉ ዝግጅቱን ከታች መከታተል ይቻላል።
11/27/202310 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

ከምስጋናው ጋ የተደረገው ሙሉ ቃለ መጠይቅ እዚህ ይገኛል

11/27/20239 minutes, 15 seconds
Episode Artwork

የአፍሪቃ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ባለፈው ቅዳሜ በሙሉ ድምፅ ከተመረጡት የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ ወሰን ጋ የተደረገ ቃለ መጠይቅ

11/20/20239 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

11/20/20239 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

11/6/202310 minutes, 23 seconds
Episode Artwork

የሆሮጉድሩ ተፈናቃዮች ሮሮ

ከኦሮሚያ ክልል፤ ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ገጠራማ ስፋራዎች በፀጥታ ችግር የተነሳ ከ2 ዓመት በፊት ተፈናቅለው አጋምሳ ከተማ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሰብአዊ ድጋፍ ባለማግኘታችን ለችግር ተጋለጥን አሉ ። ሻምቡ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ዜጎችም ነሔሴ 24 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ወደ ወረዳው ቢመለሱም ድጋፍ አለማግኘታቸውን ዐስታውቀዋል ።
10/31/20233 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

የጥቅምት 19 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በቤጂንግ ማራቶን የወንዶች ፉክክር ኢትዮጵያውያኑ ድል ሲቀናቸው፤ በሴቶች ውድድር ኬንያውያቱ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመግባት አሸንፈዋል። የደቡብ አፍሪቃ የራግቢ ብሔራዊ ቡድን በፓሪስ የዐለም ራግቢ ፍፃሜ ኒውዚላንድን ድል አድርጎ ዋንጫውን ለ4ኛ ጊዜ ወስዷል ። ማን ዩናይትድ በሜዳው ኦልትራፎርድ በማንቸስተር ሲቲ ጉድ ሆኗል ።
10/30/202310 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

ጥቅምት 19 ቀን 2016 ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

10/30/202310 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

10/16/202310 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

የሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

10/9/20239 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 28 ቀን 2016 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

ትናንት እሁድ የአሜሪካዋ ቺካጎ ያስተናገደችው የማራቶን የሩጫ ውድድር በወንዶች አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተመዝግቦበታል። በሴቶች ምድብ በተካሄደው ውድድር የተመዘገበው ሰዓትም የምንጊዜም ሁለተኛ ፈጣን ፣ የቦታው እና የአውሮጳ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። በእግር ኳስ የአምና ሻምፒዮኑ ማንችስተር ሲቲ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ሽንፈት ደርሶበታል
10/9/20239 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

10/2/202311 minutes, 8 seconds
Episode Artwork

የመስከረም 14 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ጀርመን ቤርሊን ከተማ ውስጥ ትናንት በተከናወነ የማራቶን ሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትእግስት አሰፋ የዓለም ክብረወሰን ሰብራ ለድል በቅታለች ። ከቡሩንዲ ጋር አንድ እኩል የተለያዩት ሉሲዎቹ በአፍሪቃ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታቸውንም ማክሰኞ መስከረም 15 ቀን፣ 2016 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያደርጋሉ።
9/25/202310 minutes
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

9/25/202310 minutes
Episode Artwork

የመስከረም 7 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ባሕርዳር ከነማ የእግር ኳስ ቡድን የቱኒዝያ ተጋጣሚውን ድል አድርጓል ። ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው ። ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ዩጂን በተከናወነው የዳያመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ፉክክር ክብረ ወሰን ሰብራለች ።
9/18/20239 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

9/12/20239 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

የጳጉሜ 6 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በገዛ ሜዳው የገጠመው ሽንፈት አሰልጣኙ እንዲሰናበቱ አድርጓል ። ሞ ፋራህ አራተኛ ወጥቶ ከሩጫው ዓለም በተሰናበተበው የኒውካስል የግማሽ ማራቶን ፉክክር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ አሸናፊ ሆኗል ። በሜዳ ቴኒስ የዩ ኤስ ፍጻሜ አሜሪካዊቷ ኮኮ ጋውፍ የመጀመሪያ ድሏን ተጎናጽፋ ዋንጫ አንስታለች ።
9/11/20239 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

9/4/20239 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 29 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ጀርመን ቤርሊን ከተማ ውስጥ ለድል የበቃችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ የራሷን ክብረ ወሰን ለጥቂት ሳትሰብር ቀርታለች ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ ባለቀ ሰአት በአርሰናል ብርቱ በትር ቀምሷል ። ሊቨርፑል በአንፊልድ ሜዳው ተጋጣሚው አስቶን ቪላን ዘና ብሎ አሸንፏል ። የቡንደስሊጋ፤ የላሊጋና የሴሪኣ ጨዋታዎችንም ቃኝተናል ።
9/4/20239 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 22 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮ የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር ከኦሬገኑ ያነሰ ውጤት ይዞ አጠናቋል ። የ5000 ሜትር ተፎካካሪው የአትሌት ጥላሁን ኃይሌ ጉዳይም ፌዴሬሽኑን ለበርካታ ትችቶች አጋልጧል ። በዚሁ ኢትዮጵያ ከዓለም 6ኛ ደረጃ በያዘችበት ውድድር የጀርመን ቡድን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለምንም ሜዳሊያ አጠናቋል ።
8/28/202311 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

8/28/202311 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

8/21/202311 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 15 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር መክፈቻ ኢትዮጵያውያት አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመያዝ ሜዳሊያዎቹን ተቆጣጥረዋል ። የአትሌት ሲፈን ሐሰን በውድድሩ ማብቂያ ሚዛኗን ስታ መውደቋም መነጋገሪያ ነበር ። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በስፖርቱ የገጽታ ግንባታ ላይ ቢገኝም፤ በመቶዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ዓምና በግፍ ጨፍጭፏል ተብሏል።
8/21/202311 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

8/14/202310 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 8 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ብራዚሊያዊው ኔይማር የእነ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተቀናቃኝ ቡድንን በሳዑዲ አረቢያ ሊቀላቀል ጫፍ ደርሷል ። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአል ናስር ቡድን ጋር ዋንጫ ማንሳት ችሏል ። የባየር ሙይንሽን ሽንፈት ደጋፊዎቹን አስቆጥቷል ። በሴቶች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ስፔን ከስዊድን፤ እንግሊዝ ከአውስትራሊያ ለግማሽ ፍጻሜ ነገ እና ከነገ በስትያ ይጋጠማሉ ።
8/14/202310 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

የነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

ሃንጋሪ ቡዳፔስት የምታስተናግደው የ2023 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊጀመር ከሁለት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ ብቻ ቀርቶታል ።ሽርሽር ወደ አሜሪካ የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያደረጋቸውን ሁለት የወዳጅነት ጫወታዎች ማሸነፍ ችሏል። የዓለም የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ የ4 ጊዜ አሸናፊው የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጥሎ ማለፉ ላይ ቀርቷል።
8/7/202310 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

የሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አሜሪካ ተጉዟል። በሴካፋ የእግር ኳስ ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው ከ18 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ የቡሩንዲ አቻውን ማሸነፍ ችሏል። በ 2023 የሴቶች ዓለም ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፍ የተሸጋገሩ ሃገራት እየተለዩ ናቸው።
7/31/202310 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

የሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

7/17/20239 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

የሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

7/3/20239 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

የሰኔ 19 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ትግራይ ክልል ውስጥ እሁድ ሰኔ 18 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ተጠናቋል ። ኤርትራ አስመራ ከተማ ውስጥም የኤርትራ ብሔራዊ የጎዳና ላይ የብስክሌት የፍጻሜ ፉክክር ትናንት ተከናውኗል ። ልዩ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት ጀርመን ቤርሊን ከተማ ውስጥ ተፈጽሟል ። ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችንም ቃኝተናል ።
6/26/202312 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

6/12/20239 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

6/5/202310 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

5/29/20239 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

የግንቦት 14 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ዘንድሮ አይበገሬነቱን ያስመሰከረው ማንቸስተር ሲቲ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው የፕሬሚየር ሊጉ ዋንጫን መውሰዱን አረጋግጧል ። ከሻምፒዮንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎችም ሁለት ዋንጫዎችን ለመሰብሰብ የመጨረሻ የፍጻሜ ግጥሚያዎች ብቻ ይቀሩታል ። ሊቨርፑል ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ የመግባት እድሉን አሳልፎ ሰጥቷል ።
5/22/202310 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

5/22/202310 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

ስፖርት፦ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም.

5/15/202310 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

ስፖርት፦ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም.

በዛሬው የስፖርት ዝግጅታችን አትሌቲክስ፣የሳምንቱ መጨረሻ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ክለቦች እና የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ውጤቶች እና ሌሎችም ስፖርታዊ መረጃዎች ተካተዋል። የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ አጠናቅራዋለች።
5/15/202310 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

5/1/20239 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

4/24/202310 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

የሚያዝያ 16 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያ አሸንፈው ለፍጻሜ በቅተዋል ። በፕሬሚየር ሊጉ ቶትንሀም ሆትስፐር በኒውካስል ብርቱ ሽንፈት ገጥሞታል ። ትውልደ ኤርትራዊ ስዊድናዊው አጥቂ አሌክሳንደር ይሳቅ ብቃቱን አስመስክሯል ። ባየርን ሙይንሽን ሽንፈቶችን እያስተናገደ ነው ።
4/24/202310 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

4/17/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ አርሰናል ዋንጫ የማግኝት ሰፊ እድሉን እያጠበበ ነው ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በስምምነት ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሆላንድ የሮተርዳም ማራቶን ውጤት አልቀናቸውም ። በወንዶች ፉክክር የኤርትራ ሯጭ የሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል ። ተጨማሪ ዘገባ አካተናል ።
4/17/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እና የአውሮጳ ዋና ዋና ሊጎች ውጤቶች ሲቃኙ

4/10/20237 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

4/3/202310 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
3/27/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

3/20/202310 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የየካቲት 27 ቀን 2015 ስፖርት

3/6/20239 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

የካቲት 20 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተደረጉ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል ። የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ግጥሚያዎች ነገ እና ከነገ በስትያ አምስተኛ ዙራቸው ይቀጥላሉ ። በከባድ ሚዛን የቡጢ ፍልሚያ ዝነኛው ታይሰን ፉሪ ወንድም ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በተከናወነ ግጥሚያ አሸናፊ ሆኗል ።
2/27/20239 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

2/27/20239 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

2/20/202311 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የካቲት 13 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ መጓተት በሚሊዮን የሚቆጠር የብር ብክነትን አስከትሏል። ከንድፍ አንስቶ በግንባታ ሒደቱ ከ11 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የስታዲየም ግንባታ ጉዳይ በቢሊዮን የሚቆጠር ተጨማሪ የሀገሪቱ ሀብትን አደጋ ላይ ጥሏል። ነገ እና ረቡዕ የሻምፖዮንስ ሊግ ወሳኝ ግጥሚያዎች ይኖራሉ። ሪያል ማድሪድ ከሊቨርፑል ጋር ተፋጧል።
2/20/202311 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

2/13/202310 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/30/20238 minutes, 1 second
Episode Artwork

የጥር 15 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፦ እጅግ ውብ ፉክክር በታየበት ግጥሚያ አርሰናል ማንቸስተር ዩናይትድን ድል በማድረግ ዘንድሮ ዋንጫውን ለማንሳት የቆረጠ መሆኑን ዐሳይቷል። ኧርሊንግ ኦላንድ በዘንድሮ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ለማንቸስተር ሲቲ አራተኛ ሔትትሪኩን ሠርቷል። በጀርመን ቡንደስሊጋ ቬርደር ብሬመን በኮሎኝ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።
1/23/20239 minutes, 1 second
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/23/20239 minutes, 1 second
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/16/202310 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/9/202310 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

የጥር 1 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ዘንድሮ አልጀሪያ በምታስተናግደው የአፍሪቃ ሃገራት ሻምፒዮን (CHAN) ግጥሚያ ተፎካካሪ የሚሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በምድብ «ሀ» ከሞዛምቢክ፤ አልጀሪያ እና ሊቢያ ጋር ከቀናት በኋላ ይጋጠማል። በስፔን አገር አቋራጭ የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰሎሞን ባረጋ አሸናፊ ሆኗል።
1/9/202310 minutes, 19 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/2/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 24 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ የኳስ ንጉሡ ፔሌ ስንብት ዛሬ እየተካሄደ ነው። ከዓለማችን ድንቅ ተጨዋቾች አንዱ የሆነው ፖርቹጋላዊ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለሳዑዲ ዓረቢያው አል ናስር መፈረሙ ቡድኑን በማኅበራዊ መገናኛ አውታር እጅግ ዝነኛ አድርጎታል። አትሌቲክስ እና ሌሎች የስፖርት መረጃዎንም አካተናል።
1/2/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

1/2/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

የታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

ዓለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ የሀገራት አዲስ የደረጃ ሰንጠዥ ይፋ አድርጓል፤ ብራዚል ደረጃውን ትመራለች ። ከዓለም ዋንጫው መለስ የታላላቅ ሊጎች ውድድሮች ተጀምረዋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ የቦክሲንግ ዴይ ጫወታዎችን አመሻሹን ቀን 9 ሰአት ተኩል በተጀመረ ጫወታ ተጀምሯል።
12/26/20227 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/19/202212 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

የታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

አርጀንቲናን ከ36 ዓመታት በኋላ ለዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የፍጻሜ ድል ያበቃው የትናንቱ ግጥሚያና የአዘጋጇ ካታር መዝጊያ ሥርዓት እጅግ አስደማሚ ነበር። የሐትሪክ ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ ይስሐቅ በላይ የፍጻሜ ጨዋታ ትናንት በተኪያሄደበት ስታዲየም ታድሞ ነበር። ስለመዝጊያ ስርዓቱ እና በካታር ቆይታው ስለታዘበው ስፖርታዊ ክንውኖች ጠይቀነዋል።
12/19/202212 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/12/202210 minutes, 35 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

12/5/20229 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

የኅዳር 26 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በዓለም ዋንጫ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የተደረጉ ጨዋታዎች በምድብ የዙር ጨዋታዎች እንደነበሩት ብዙም ሳያጓጉ አሸናፊዎቹ በጊዜ ዕየታወቁ ተጠናቀዋል። የጃፓንና ከክሮሺያ ጨዋታ ተራዝሟል። ስፔን ቫለንሺያ ውስጥ ትናንት በተከናወነው የማራቶን ሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያውያቱ አትሌቶች ለድል ሲበቁ በወንዶች ውድድር ኬንያውያን እና የታንዛኒያ ሯጭ ቀንቷቸዋል።
12/5/20229 minutes, 38 seconds