Winamp Logo
ባህላዊ ጉዳዮች | Deutsche Welle Cover
ባህላዊ ጉዳዮች | Deutsche Welle Profile

ባህላዊ ጉዳዮች | Deutsche Welle

Amharic, Arts, 1 season, 54 episodes, 12 hours, 52 minutes
About
ሳምንታዊው የባህል መድረክ በተለይ የኪነ-ጥበብ ስራዎች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሰፋ ብለው የሚታዩበት መድረክ ነው።
Episode Artwork

ዓለም አቀፉ የኢትዮጰያ ህብረተሰብ ልማት ድርጅት 40ኛ ዓመት ምስረታ

«ECDC ሰዉ ሲሰደድ መጀመርያ ቦታ የሚያይበት፤ ንግድ ሲያምረዉ ንግድ ከፍቶ የሚቋቋምበት፤ ትዳር ሲፈልግ ባሉት አዳራሾች ዉስጥ የሚዳርበት የሚኳልበት፤ ሐዘን ቢገጥመዉ ደግሞ አንገቱን ደፍቶ፤ እዝንተኛዉን የሚያስተናግድበት፤ ለህብረተሰቡ ትልቅ ጥቅም የሰጠ ድርጅት ነዉ ሲሉ አንድ በድርጅቱ 26ኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ ሰዉ ተናግረዋል»
9/14/202314 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ECDC በአክሱም ከተማ ጨምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመማርያ መጻሐፍትን እና ኮንፒዉተሮችን በመላክ፤ ቤተ መጽሐፍትን በማቋቋም ይረዳል

9/14/202314 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ተፈናቃዮችና አዲስ ዓመት በመቐለ

ተሰናባቹ 2015 በትግራይ ካለፉት ዓመታት የቀጠለ ጦርነት የነበረበት፣ በዚያው በአሮጌው ዓመት ደም አፋሳሹ ጦርነት ያስቆመ ስምምነት የተደረሰበት እና የሰላም ተስፋ የተፈጠረበትነበረ። ለረዥም ግዜ ተዘግተው የነበሩ የስልክ እና ኢንተርኔት ጨምሮ የተለያዩ የህዝብ አገልግሎቶች ዳግም የተጀመሩበት ነበር።
9/12/20233 minutes, 17 seconds
Episode Artwork

ድንቅ የዓፋር እናቶች የፈጠራ ውጤት

ሐለዋ የሚባል ዛፍ አለ። እሱ እንደፈለግክ የሚተጣጠፍ ነው።በዚህ እንጨት የቤቱ ቅርጽ ተሰርቶ ካበቃ ቦኋላ ከዘንባባ ዛፍ ከሚሰራው ሰሌን ጣራውና ግድግዳው ይለብሳል። በዚህ መልኩነው የሚሰራው።
9/7/202311 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶም ቦምብ ጥቃት 78ኛ ዓመት

ሂሮሽማና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ አሜሪካ አዉቶም ቦንቦችዋን የጣለችበት አሰቃቂ ጥቃት ዘንድሮ ለ 78ኛ ጊዜ ታስቧል። ቀኑ ወደ 200 ሺህ በላይ ህዝብ ያለቀበት እለት የታሰበበት ብቻ ሳይሆን፤ በዓለም ዙርያ የአቶም ጦር መሳርያ አስከፊነትን የሚያንፀባርቁ ሰላማዊ ሰልፎችም የተካሄዱበትም ነበር። የሰዉ ልጅ ዛሬስ የጦርነትን አስከፊነት ተረድቷል?
8/25/202313 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶም ቦምብ ጥቃት 78ኛ ዓመት መታሰብያ

8/24/202313 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሜሪያም ደስታ፤ እርሶ ከፈለጉና ጠንክረው ከሰሩ የማይለወጡበት ምንም ምክንያት የለም

ኑሮዋን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገችዉ ወጣትዋ ሜሪያም ደስታ ለኢትዮጵያዉያን የማማከር ወይም የኮቺንግ አገልግሎት በመስጠትዋ ትታወቃለች። ኮቺንግ አቻ ትርጉም አላገኘሁለትም የምትለዉ ሜሪያም ደስታ፤ የስብዕና እድገት አሰልጣኝ በሜልም ነዉ ትታወቃለች። ሜሪያም ደስታ በዚህ አገልግሎትዋ ዓመታትን አስቆጥራለች።
8/17/202314 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ኑሮዋን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገችዉ ወጣትዋ ሜሪያም ደስታ ለኢትዮጵያዉያን የማማከር ወይም የኮቺንግ አገልግሎት በመስጠትዋ ትታወቃለች።

8/17/202314 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ለዓባይ ወንዝ ክብር የሰጠዉ የሙዚቃ ድግስና ባለመሰንቆዉ አርቲስት ሀዲስ ዓለማየሁ «ሀዲንቆ»

በሆላንድ አምስተርዳም፤ ለዓባይ ወንዝ ክብር የሰጠዉ ኮንሰርት ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈዉ አርቲስት ሀዲስ ዓለማየሁ፤ ሀዲንቆ መድረኩን ተቆጣጥሮት ነበር። መድረክ የአረቦች የሙዚቃ እና የዳንስ ፌስቲቫልን የሚያዘጋጀዉ ሱክ የተባለዉ ድርጅት ነዉ። መነሻዉ ኢትዮጵያ የሆነዉ የዓባይ ወንዝ ለ 400 ሚሊዮን ህዝብ የኑሮ ቁልፍ ነዉ።
8/11/202315 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

ለዓባይ ወንዝ ክብር የሰጠዉ የሙዚቃ ድግስና ባለመሰንቆው አርቲስት ሀዲስ ዓለማየሁ

8/10/202315 minutes, 26 seconds
Episode Artwork

ቆይታ ከመምህርት እፀገነት ከበደ ጋር

8/3/202315 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

ህጸጽን በሽሙጥ፤ በእፀገነት ከበደ

መምህርት እፀገነት ከበደ ትባላለች። ባለትዳር የልጆች እናት ናት። ጎልማሳዋ የሥነ-ጽሑፍ ባለሞያ፤ አዝናኝ ፈገግ የሚያሰኙ ግን ደግሞ የማህበረሰብ እፀጽ ነቅሶ በማዉጣት በወግ መልክ በዩትዩብ በቲክቶክ ብሎም አዲስ አበባ ዉስጥ በተለያዩ መድረኮች በማቅረቧ ትታወቃለች።
8/3/202315 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

የ2023 የአፍሪቃ ዘመናዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ተሸላሚዋ ወጣት

ወጣቷ የተሸለመችው «በትላንት እና በነገ መካከል» በተሰኜ የፎቶግራፊ ስራዋ ነው
7/27/202314 minutes, 12 seconds
Episode Artwork

የዎላይታ ባህላዊ ሙዚየምን በጨረፍታ

7/13/20239 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

ዲያስፖራ ጎረቤቶቼ

«እኛ ኢትዮጵያዉያን ከሀገር ወጥተን ለመኖር ያለን ተስፋ፤ የማይጨበጥ ሃሳብ በጣም ያስገርመኛል። እንኳን እኛ፤ በርበሬ ሚጥሚጣ፤ ሽሮዋችን፤ ከሀገር ሲወጣ አያምርበትም፤ ይበላሻል። በርበሬዉ ዱቄቱ ይነጣል። ከሀገር መዉጣትን እንደመፍትሄ፤ ማስወጣትን እንደመፍትሄ ፤ መራቅን እንደመፍትሄ አድርገን ነዉ የምንወስደዉ። ለምን ?»
7/6/202315 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

«እንኳን እኛ፤ በርበሬ ሚጥሚጣ፤ ሽሮዋችን፤ ከሀገር ሲወጣ አያምርበትም፤ ይበላሻል። በርበሬዉ ዱቄቱ ይነጣል»

7/6/202315 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

ፊልሙ የሁለት ጓደኛሞች የህይወት ዉጣ ዉረድ ብሎም ትግልና የዓላማ ጽናትን ይተርካል

6/29/202314 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

«የንፋሱ ፍልሚያ» የመጀመርያዉ በዓለም አቀፍ ለዉድድር የቀረበ ፊልም

“በእውነተኛ ሁኔታ ላይ የተመሰረተዉ ፊልም ነዉ።በአዲስ አበባ የጎዳና ሕይወትን አሰቃቂና አሳዛኝ ገጽታን የሚያንፀባርቅ፤ ብሎም በከባድና በአስጨናቂ ጊዜዎች ሁሉ ጸንቶ መቆም የቻለ ጓደኝነትና በጥንካሪ ህልም እና ምኞት ስኬትን ማግኘታቸዉን ያንፀባርቃል ነዉ። ፊልሙ በጣም አዎንታዊ መልክት ያዘለና ለኢትዮጵያ አዎንታዊ አቀራረብ ያለው ፊልም ነው።»
6/29/202314 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

«የቱሪስቶች መዳራሻና የአገር በጎ ገጽ ግንባታ ማዕከል፣ ይፍረስ መባሉ ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗል።»

6/22/202313 minutes, 16 seconds
Episode Artwork

«በአሁኑ ወቅት ኪነ-ጥበቡ አደርባይ እንዲሆን ነዉ የተደረገዉ»

6/15/202315 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ድምፅ አልባዉ የኪነ-ጥበብ ጥሪ

በአሁን ጊዜ ኪነ- ጥበቡ አፉን ለግሞ ቁጭ ብሏል። ኪነ-ጥበቡ ማድረግ ያለበትን ቢያደርግ ኖሮ መንግሥትንም ይጠቅመዉ ነበር። ኪነ-ጥበቡ መንግሥትን እንዲያወድሰዉ ብቻ ሳይሆን እንዲተቸዉ አቅም መፍጠር አለበት። ግን እየሆነ ያለዉ ኪነ-ጥበቡ አደርባይ እንዲሆን ነዉ የተደረገዉ። በአሁኑ ሰዓት ግን ኪነ-ጥበቡ አፉን ተይዟል።
6/15/202315 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ሰላም ኢትዮጵያ የአፍሪቃ መንግሥታት ከብሔራዊ በጀታቸዉ ቢያንስ 1% ለኪነ-ጥበብ፤ ባህልና፤ ቅርስ ዘርፎች እንዲመድቡ ጠየቀ

6/8/202314 minutes, 8 seconds
Episode Artwork

”ሰላም ኢትዮጵያ” የአፍሪቃ ሃገራት ለኪነጥበብ እንዲበጅቱ ጠየቀ

አፍሪቃ በተለያዩ ባህሎች ዘርፍ ግዙፍ እና እምቅ ኃብት ያላት ግን እስካሁን እንብዛም ያልተጠቀመችበት እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። ከአፍሪቃ ህብረት ጋር የጀመርነዉ ፕሮጀክት አዲስ የሚያደርገዉ የአፍሪቃ ሃገራት ከብሔራዊ ገቢያቸዉ 1% ን የኪነጥበብ እንዲያዉሉ መጠየቁ ነዉ። ህብረቱም አፍሪቃዉያቱ ሃገራት ይህን እንዲያደርጉ ወስኗል።
6/8/202314 minutes, 8 seconds
Episode Artwork

«ክቡር አቶ ከተማ ይፍሩ የአፍሪቃ አንድነት ዋና ጽ/ቤት ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ላይ እንዲሆን ያደረጉ ጀግና ዲፕሎማት ነበሩ»

6/1/202315 minutes, 11 seconds
Episode Artwork

ያልተነገረላቸዉ የአፍሪቃ አንድነት መስራችና ዲፕሎማት

ክቡር አቶ ከተማ ይፍሩ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸዉ ብርቅዬ ልጆች አንዱ ናቸዉ። አፍሪቃዉያን ወንድምና እህቶቻችን ናቸዉ፤ የኛ የብቻ ነጻነት ዋጋ የለዉም ይሉ ነበር። ለአህጉር አፍሪቃ የሚያስቡ ፓን አፍሪካኒስት ነበሩ። እንደ ኔልሰን ማንዴላ፤ ኬኔት ካዉንዳ ያሉ የአፍሪቃ ታጋዮችን ኢትዮጵያ እንድትረዳ ያደረጉ ናቸዉ። እነሱም መጨረሻ ከልብ አመስግነዋል።
6/1/202315 minutes, 11 seconds
Episode Artwork

ፊላ የደራሼ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ

በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ የተለያዩ ብሄረሰቦች ካላቸው ባህላዊ አሴቶች መካከል ነባር የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸው ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ ከእነኝህም መካከል ፊላ በመባል የሚታወቀው የደራሼ ብሄር ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ አንዱ ነው ፡፡ ፊላ ከትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያዎች የሚመደብ ነው፡፡ አጨዋወቱም በጋራ ሲሆን የተለየ ህብረ ድምፃዊ ቃናን ይሰጣል፡፡
5/25/20239 minutes, 23 seconds
Episode Artwork

የዶቼ ቬለ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎች በጀርመን

የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል ጋዜጠኞች ለጥቂት ቀናት ስልጠና ዶቼ ቬለ ዋና መስርያ ቤት ይገኛሉ። የዶቼ ቬለ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሰለሞን ሙጬ፤ የባህርዳሩ ዘጋቢ ዓለምነዉ መኮንን እና የሃዋሳዉ ዘጋቢ ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ቦን በሚገኘዉ ቆይታቸዉ የጋዜጠኝነት አሰራር ደንብን ብሎም የድምጽና የምስል ቀረጻ ደንብና አሰራሮችን ስልጠና ወስደዋል።
5/22/202313 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

«እንደ የዶይቸ ቬለ ጋዜጠኛ በስራችን ገለልተኛ ብሎም ሥነ-ምግባሩንም በማክበር ነው» የዶቼ ቬለ ዘጋቢዎች

5/18/202313 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ከ10ኛዉ ክፍለ ዘመን የጀመረዉ የብሪታንያ ንጉሳዊ ሥርዓት

የብሪታንያ ንጉሳዊ ቤተሰብ በጭራሽ ፖለቲካ ዉስጥ አይገባም። ዘዉድ የሃገሪቱ ባህል የአንድነትና የሃገሪቱ የህልዉና ምልክት ነዉ። ሥነ-ስርዓቱ በጣም አስደሳች ነበር። በታላቅዋ ብሪታንያ ይህ የንጉሳዉያን አስተዳደር ባይኖር ኖሮ፤ ምናልባትም ስኮትላንድ፤ ዌልዝ፤ እንዲሁም ሰሜናዊ አየርላንድ ከብሪታንያ ዉስጥ ከብዙ ዓመታት በፊት በወጡ ነበር።
5/11/202314 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

“ገበታ ለወገኔ” በስዊዘርላን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተሳትፎ

በስዊዘርላንድ ኢትዮጵያዉያንን ያሰባሰበዉ “ገበታ ለወገኔ” የተባለዉ በጎ አድራጎት ድርጅት፤ ስለ ኢትዮጵያ ያገባናል፤ ኃላፊነትም አለብን በሚል መርህ በኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ ከጀመረ ዓመታትን አስቆጥሯል። ለህዝባችን በተለይ ጦርነት ላደቀዉ ህዝብ መድረስ ከማንም በላይ የኛ ኢትዮጵያዉያን ቀዳሚ ኃላፊነት እና ግዴታ ነዉ።
5/4/202315 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

“ገበታ ለወገኔ” በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በጎ አድራጎት

5/4/202315 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

የሲዳማ ማህበረሰብ እና ባህሉ

4/27/202314 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ፌቼ ጫምባላላ-የሲዳማ ህዝብ የአንድነት ምልክት

ሲዳማ ክልል ህዳር 14 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ከተመሰረተ ዘንድሮ ሁለተኛ ዓመቱን ይዝዋል። የሲዳማ ህዝብ ዘንድሮ የዘመን መለወጫዉን «ፊቼ ጨንበላላ» በተለይ በድምቀት አክብሯል። ህዝቡ ክልሉን ካገኘ ወዲህ ሁሉ ነገር ሆኖለታል፤ ተሳክቶለታል ማለት አይደለም፤ ቢሆንም ግን ህዝቡ በዓሉን በሰላማዊ መንገድ ማክበሩ ትልቅ ነገር ነዉ።
4/27/202314 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

በገና እና የሁዳዴ ጾም

4/13/202312 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የዓፋሮች ባሕላዊ ጋብቻ

4/6/202313 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

15ኛዉ የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ማን ናቸዉ?

“ባንዲራችንን እንኳን እኛ ግመሎቻችንን ያውቋታል” በሚል አነጋገር የአፋር ህዝቦች ይታወቃሉ። በተለይ በዚህ ንግግራቸዉ የባንዲራን እና የአገር ፍቅርን ይበልጥ የገለፁት 9ኛዉ የአፋር ሱልጣኔት አሊሚራህ ሀንፍሬ ናቸዉ። ልጃቸዉ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ሱልጣን አንፍሬ አሊሚራህ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኃላ 15ኛ ሱልጣን ሆነዉ ተሾመዋል።
3/30/202314 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

«የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ዋርካ ነው የወደቀው» የባህል መድረክ

3/9/202314 minutes, 9 seconds
Episode Artwork

አድዋ እንዴት ይዘከር?

አድዋ ሲዘከር የአጼ ምኒሊክ እና የጦር አበጋዞቻቸው ተክለ ስብዕና ዘመን ተሻግሮ ያወዛግባል። ከ127 ዓመታት በፊት ለነጻነታቸው ቀናዒ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የተገኘው ድል ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የተሳተፉበት ነው። ታዲያ የአድዋ ዝክር ለምን ያወዛግባል? ወደፊትስ እንዴት ይዘከር?
3/2/202314 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

አድዋ እንዴት ይዘከር?

3/2/202314 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

የታሪክ ተመራማሪዉ ሐንሳሞ ሐመላ ሲታወሱ

የታሪክ ተመራማሪው ሐንሳሞ ሐመላ የሚታወቁት በ1966 ዓ.ም ያሳተሙት እና ከ 1966 ዓ.ም በፊት ስለ ደራሼ ህዝብ ማንነት የሚገልፀዉ "የድራሼ ህዝብ ታሪክ" በተባለዉ መጽሐፋቸዉ ነዉ። የአቶ ይህ መጽሐፉ ስለ ድራሼ ህዝብ ታሪክ፤ ትውፊት፤ ባህል፤ ቋንቋ፤ የኢኮኖሚያዊ መሰረት እና ትስስር ብሎም ስለ ቀጣዩ የድራሼ የኢኮኖሚ ስጋት ጭምር ያሳያል።
2/23/202315 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

የታሪክ ተመራማሪዉ ሐንሳሞ ሐመላ እንዴት ይታወሳሉ?

2/23/202315 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

ቅርሶቻችን በባዕድ ሃገር ሲቀሩ ልንቆጭ ይገባናል

2/16/202314 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ለመቀበል ዝግጁ ነን?

ቅርሶቻችን በባዕድ ሃገር ሲቀሩ ልንቆጭ ይገባናል። ስለዚህ የተዘረፉ ጥንታዊ ቅርሶቻችን ወደ ሃገር አስመልሰን በጥንቃቄ እንዲቀመጡ መንግሥት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ። ቅርሶች የጋራ መለያዎቻችንና የጋራ ሃብቶቻችን ናቸዉ። ቅርሶች የአማራ የትግሬ የኦሮሞ ወይም የሌላ ብሄር ብሄረሰቦች የግል ሃብት ሳይሆን የሃገር ሃብት፤ የሃገር ታሪክ ናቸዉ።
2/16/202314 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ዓለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ ምንድን ነው?

በዓለም አቀፍ ደረጃ እለቱ ጥር 27 ቀን 2006 ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ ሲታሰብ፤ የወቅቱ የተመድ ዋና ፀሐፊ የነበሩት ኮፊ አናን "ይህ አሳዛኝ ክስተት ሊታረም የማይችል ነው። የሰው ልጅ ግን ይህንን ሁኔታ በኀፍረትና ፀፀት በማስታወስ ከአሰቃቂ ሁኔታ ራሱን ሊታደግ እና ሊያነቃ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። በጀርመን ከ 1996 ዓመት ጀምሮ ይታሰባል።
2/2/202315 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

ዉሎ አዳር ከጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ጋር

ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ኢትዮጵያን ከደቡብ እስከ ሰሜን ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ተጉዛ፤ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ጎብኝታ፤ ባህላቸዉን ተዋዉቃ ኑሮአቸዉን ኖራ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለህዝብ «ዉሎ አዳር» በሚል ፕሮግራምዋ ከባልደረቦችዋ ጋር አቀናብራ ለሃገር የምታሳየዉ የአገርህን እወቅ ዝግጅቷ ታዋቂነትንና ተወዳጅነትን አትርፋለች።
1/26/202315 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

ዉሎ አዳር ከጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ ጋር

1/26/202315 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ ከጎርጎረሳዉያኑ 1976 ጀምሮ አዳዲስ እድሎችን ማፈላለግ የጀመርኩባት ሃገር ናት

1/19/202314 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ጀርመናዊትዋ፤ ለኢትዮጵያ በመስራት ማመስገን እፈልጋለሁ

ስራ በጀመርኩበት እድሜ ክልል ያሉ አዲሶቹን ትዉልዶች በመርዳትና በማገዝ የተደረገልኝን ነገር ሁሉ መልሼ መስጠት እፈልጋለሁ። መልሼ በመክፈል ማመስገን እፈልጋለሁ። ለብዙ ዓመታት ኢትዮጵያዉያን ሃገር ዉስጥ ያሉም ሆነ በዉጭ የሚኖሩ እዚህም ጀርመን ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ያገኘሁትን ትልቅ ጉልበት ያለዉ አወንታዊ ድጋፍ መልሼ መስጠት እፈልጋለሁ።
1/19/202314 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ጎንደር ፣ ደቡብ ትግራይ ፣ በተወሰነ የጎጃም ክፍል እንዲሁም ሰሜን ውሎ ቤተ-እስራኤላዉያን ይኖራሉ

1/12/202313 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

ባሕላዊ የግጭት አፈታት በሱሪና በሸኮ ብሔረሰቦች

1/5/202312 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

የዘንድሮዉ ክብረ በዓል የዩክሬኑ ጦርነት ጥላ አጥሎበት አልፏል

12/29/202215 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

የጀርመናዉያን የገና በዓል ባህላዊ አከባበር

የገና በዓል በጀርመን ድሆች የሚጠየቁበት ለሌላቸዉ ያለሽን የምታካፍይበት የተባረከ እና የተደነቀ ሰዓትነዉ የገና በዓላቸዉን እኔም እወደዋለሁ። በዚህ ዓመት በዩክሬይን እና የሩስያ ጦርነት ምክንያት የገና በዓል ጥቁር ጥላ ያንዣበበበት ነበር። አዉሮጳን ችግር እና ሃሳብ ላይ ጥሏል።
12/29/202215 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

የአፍሪቃ የኳስ አባት ክቡር ይድነቃቸዉ ተሰማን ሞሮኮ አክብራቸዋለች

12/15/202215 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

የአፍሪቃ የእግር ኳስ አባትና የሞሮኮ የኳስ ጥበብ

ኢትዮጵያን ጨምሮ 11 የአፍሪቃ አገራት ያደረጉትን የማጣሪያ ውድድር አሸንፋ በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ1970 ዓ.ም በሜክሲኮ የዓለም ዋንጫ አፍሪቃን ወክላ የተካፈለች የመጀመሪያዋ አገር ሞሮኮ ነበረች። ሞሮኮ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፖርቱጋልን ገጥማ አንድ ለዜሮ አሸንፋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ በማለፍም የመጀመሪያዋ አፍሪቃ አገር ሆናለች፡፡
12/15/202215 minutes, 42 seconds