ዓለም አቀፉ የኢትዮጰያ ህብረተሰብ ልማት ድርጅት 40ኛ ዓመት ምስረታ
«ECDC ሰዉ ሲሰደድ መጀመርያ ቦታ የሚያይበት፤ ንግድ ሲያምረዉ ንግድ ከፍቶ የሚቋቋምበት፤ ትዳር ሲፈልግ ባሉት አዳራሾች ዉስጥ የሚዳርበት የሚኳልበት፤ ሐዘን ቢገጥመዉ ደግሞ አንገቱን ደፍቶ፤ እዝንተኛዉን የሚያስተናግድበት፤ ለህብረተሰቡ ትልቅ ጥቅም የሰጠ ድርጅት ነዉ ሲሉ አንድ በድርጅቱ 26ኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ ሰዉ ተናግረዋል»
9/14/2023 • 14 minutes, 56 seconds ECDC በአክሱም ከተማ ጨምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመማርያ መጻሐፍትን እና ኮንፒዉተሮችን በመላክ፤ ቤተ መጽሐፍትን በማቋቋም ይረዳል
9/14/2023 • 14 minutes, 56 seconds ተሰናባቹ 2015 በትግራይ ካለፉት ዓመታት የቀጠለ ጦርነት የነበረበት፣ በዚያው በአሮጌው ዓመት ደም አፋሳሹ ጦርነት ያስቆመ ስምምነት የተደረሰበት እና የሰላም ተስፋ የተፈጠረበትነበረ። ለረዥም ግዜ ተዘግተው የነበሩ የስልክ እና ኢንተርኔት ጨምሮ የተለያዩ የህዝብ አገልግሎቶች ዳግም የተጀመሩበት ነበር።
9/12/2023 • 3 minutes, 17 seconds ሐለዋ የሚባል ዛፍ አለ። እሱ እንደፈለግክ የሚተጣጠፍ ነው።በዚህ እንጨት የቤቱ ቅርጽ ተሰርቶ ካበቃ ቦኋላ ከዘንባባ ዛፍ ከሚሰራው ሰሌን ጣራውና ግድግዳው ይለብሳል። በዚህ መልኩነው የሚሰራው።
9/7/2023 • 11 minutes, 51 seconds የሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶም ቦምብ ጥቃት 78ኛ ዓመት
ሂሮሽማና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ አሜሪካ አዉቶም ቦንቦችዋን የጣለችበት አሰቃቂ ጥቃት ዘንድሮ ለ 78ኛ ጊዜ ታስቧል። ቀኑ ወደ 200 ሺህ በላይ ህዝብ ያለቀበት እለት የታሰበበት ብቻ ሳይሆን፤ በዓለም ዙርያ የአቶም ጦር መሳርያ አስከፊነትን የሚያንፀባርቁ ሰላማዊ ሰልፎችም የተካሄዱበትም ነበር። የሰዉ ልጅ ዛሬስ የጦርነትን አስከፊነት ተረድቷል?
8/25/2023 • 13 minutes, 32 seconds ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶም ቦምብ ጥቃት 78ኛ ዓመት መታሰብያ
8/24/2023 • 13 minutes, 32 seconds ሜሪያም ደስታ፤ እርሶ ከፈለጉና ጠንክረው ከሰሩ የማይለወጡበት ምንም ምክንያት የለም
ኑሮዋን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገችዉ ወጣትዋ ሜሪያም ደስታ ለኢትዮጵያዉያን የማማከር ወይም የኮቺንግ አገልግሎት በመስጠትዋ ትታወቃለች። ኮቺንግ አቻ ትርጉም አላገኘሁለትም የምትለዉ ሜሪያም ደስታ፤ የስብዕና እድገት አሰልጣኝ በሜልም ነዉ ትታወቃለች። ሜሪያም ደስታ በዚህ አገልግሎትዋ ዓመታትን አስቆጥራለች።
8/17/2023 • 14 minutes, 59 seconds ኑሮዋን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገችዉ ወጣትዋ ሜሪያም ደስታ ለኢትዮጵያዉያን የማማከር ወይም የኮቺንግ አገልግሎት በመስጠትዋ ትታወቃለች።
8/17/2023 • 14 minutes, 59 seconds ለዓባይ ወንዝ ክብር የሰጠዉ የሙዚቃ ድግስና ባለመሰንቆዉ አርቲስት ሀዲስ ዓለማየሁ «ሀዲንቆ»
በሆላንድ አምስተርዳም፤ ለዓባይ ወንዝ ክብር የሰጠዉ ኮንሰርት ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈዉ አርቲስት ሀዲስ ዓለማየሁ፤ ሀዲንቆ መድረኩን ተቆጣጥሮት ነበር። መድረክ የአረቦች የሙዚቃ እና የዳንስ ፌስቲቫልን የሚያዘጋጀዉ ሱክ የተባለዉ ድርጅት ነዉ። መነሻዉ ኢትዮጵያ የሆነዉ የዓባይ ወንዝ ለ 400 ሚሊዮን ህዝብ የኑሮ ቁልፍ ነዉ።
8/11/2023 • 15 minutes, 26 seconds ለዓባይ ወንዝ ክብር የሰጠዉ የሙዚቃ ድግስና ባለመሰንቆው አርቲስት ሀዲስ ዓለማየሁ
8/10/2023 • 15 minutes, 26 seconds 8/3/2023 • 15 minutes, 7 seconds መምህርት እፀገነት ከበደ ትባላለች። ባለትዳር የልጆች እናት ናት። ጎልማሳዋ የሥነ-ጽሑፍ ባለሞያ፤ አዝናኝ ፈገግ የሚያሰኙ ግን ደግሞ የማህበረሰብ እፀጽ ነቅሶ በማዉጣት በወግ መልክ በዩትዩብ በቲክቶክ ብሎም አዲስ አበባ ዉስጥ በተለያዩ መድረኮች በማቅረቧ ትታወቃለች።
8/3/2023 • 15 minutes, 7 seconds የ2023 የአፍሪቃ ዘመናዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ተሸላሚዋ ወጣት
ወጣቷ የተሸለመችው «በትላንት እና በነገ መካከል» በተሰኜ የፎቶግራፊ ስራዋ ነው
7/27/2023 • 14 minutes, 12 seconds 7/13/2023 • 9 minutes, 37 seconds «እኛ ኢትዮጵያዉያን ከሀገር ወጥተን ለመኖር ያለን ተስፋ፤ የማይጨበጥ ሃሳብ በጣም ያስገርመኛል። እንኳን እኛ፤ በርበሬ ሚጥሚጣ፤ ሽሮዋችን፤ ከሀገር ሲወጣ አያምርበትም፤ ይበላሻል። በርበሬዉ ዱቄቱ ይነጣል። ከሀገር መዉጣትን እንደመፍትሄ፤ ማስወጣትን እንደመፍትሄ ፤ መራቅን እንደመፍትሄ አድርገን ነዉ የምንወስደዉ። ለምን ?»
7/6/2023 • 15 minutes, 20 seconds «እንኳን እኛ፤ በርበሬ ሚጥሚጣ፤ ሽሮዋችን፤ ከሀገር ሲወጣ አያምርበትም፤ ይበላሻል። በርበሬዉ ዱቄቱ ይነጣል»
7/6/2023 • 15 minutes, 20 seconds ፊልሙ የሁለት ጓደኛሞች የህይወት ዉጣ ዉረድ ብሎም ትግልና የዓላማ ጽናትን ይተርካል
6/29/2023 • 14 minutes, 54 seconds «የንፋሱ ፍልሚያ» የመጀመርያዉ በዓለም አቀፍ ለዉድድር የቀረበ ፊልም
“በእውነተኛ ሁኔታ ላይ የተመሰረተዉ ፊልም ነዉ።በአዲስ አበባ የጎዳና ሕይወትን አሰቃቂና አሳዛኝ ገጽታን የሚያንፀባርቅ፤ ብሎም በከባድና በአስጨናቂ ጊዜዎች ሁሉ ጸንቶ መቆም የቻለ ጓደኝነትና በጥንካሪ ህልም እና ምኞት ስኬትን ማግኘታቸዉን ያንፀባርቃል ነዉ። ፊልሙ በጣም አዎንታዊ መልክት ያዘለና ለኢትዮጵያ አዎንታዊ አቀራረብ ያለው ፊልም ነው።»
6/29/2023 • 14 minutes, 54 seconds «የቱሪስቶች መዳራሻና የአገር በጎ ገጽ ግንባታ ማዕከል፣ ይፍረስ መባሉ ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗል።»
6/22/2023 • 13 minutes, 16 seconds «በአሁኑ ወቅት ኪነ-ጥበቡ አደርባይ እንዲሆን ነዉ የተደረገዉ»
6/15/2023 • 15 minutes, 4 seconds በአሁን ጊዜ ኪነ- ጥበቡ አፉን ለግሞ ቁጭ ብሏል። ኪነ-ጥበቡ ማድረግ ያለበትን ቢያደርግ ኖሮ መንግሥትንም ይጠቅመዉ ነበር። ኪነ-ጥበቡ መንግሥትን እንዲያወድሰዉ ብቻ ሳይሆን እንዲተቸዉ አቅም መፍጠር አለበት። ግን እየሆነ ያለዉ ኪነ-ጥበቡ አደርባይ እንዲሆን ነዉ የተደረገዉ። በአሁኑ ሰዓት ግን ኪነ-ጥበቡ አፉን ተይዟል።
6/15/2023 • 15 minutes, 4 seconds ሰላም ኢትዮጵያ የአፍሪቃ መንግሥታት ከብሔራዊ በጀታቸዉ ቢያንስ 1% ለኪነ-ጥበብ፤ ባህልና፤ ቅርስ ዘርፎች እንዲመድ ቡ ጠየቀ
6/8/2023 • 14 minutes, 8 seconds ”ሰላም ኢትዮጵያ” የአፍሪቃ ሃገራት ለኪነጥበብ እንዲበጅቱ ጠየቀ
አፍሪቃ በተለያዩ ባህሎች ዘርፍ ግዙፍ እና እምቅ ኃብት ያላት ግን እስካሁን እንብዛም ያልተጠቀመችበት እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። ከአፍሪቃ ህብረት ጋር የጀመርነዉ ፕሮጀክት አዲስ የሚያደርገዉ የአፍሪቃ ሃገራት ከብሔራዊ ገቢያቸዉ 1% ን የኪነጥበብ እንዲያዉሉ መጠየቁ ነዉ። ህብረቱም አፍሪቃዉያቱ ሃገራት ይህን እንዲያደርጉ ወስኗል።
6/8/2023 • 14 minutes, 8 seconds «ክቡር አቶ ከተማ ይፍሩ የአፍሪቃ አንድነት ዋና ጽ/ቤት ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ላይ እንዲሆን ያደረጉ ጀግና ዲፕሎማት ነበሩ»
6/1/2023 • 15 minutes, 11 seconds ያልተነገረላቸዉ የአፍሪቃ አንድነት መስራችና ዲፕሎማት
ክቡር አቶ ከተማ ይፍሩ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸዉ ብርቅዬ ልጆች አንዱ ናቸዉ። አፍሪቃዉያን ወንድምና እህቶቻችን ናቸዉ፤ የኛ የብቻ ነጻነት ዋጋ የለዉም ይሉ ነበር። ለአህጉር አፍሪቃ የሚያስቡ ፓን አፍሪካኒስት ነበሩ። እንደ ኔልሰን ማንዴላ፤ ኬኔት ካዉንዳ ያሉ የአፍሪቃ ታጋዮችን ኢትዮጵያ እንድትረዳ ያደረጉ ናቸዉ። እነሱም መጨረሻ ከልብ አመስግነዋል።
6/1/2023 • 15 minutes, 11 seconds በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ የተለያዩ ብሄረሰቦች ካላቸው ባህላዊ አሴቶች መካከል ነባር የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸው ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ ከእነኝህም መካከል ፊላ በመባል የሚታወቀው የደራሼ ብሄር ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ አንዱ ነው ፡፡ ፊላ ከትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያዎች የሚመደብ ነው፡፡ አጨዋወቱም በጋራ ሲሆን የተለየ ህብረ ድምፃዊ ቃናን ይሰጣል፡፡
5/25/2023 • 9 minutes, 23 seconds የዶቼ ቬለ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎች በጀርመን
የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል ጋዜጠኞች ለጥቂት ቀናት ስልጠና ዶቼ ቬለ ዋና መስርያ ቤት ይገኛሉ። የዶቼ ቬለ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሰለሞን ሙጬ፤ የባህርዳሩ ዘጋቢ ዓለምነዉ መኮንን እና የሃዋሳዉ ዘጋቢ ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ቦን በሚገኘዉ ቆይታቸዉ የጋዜጠኝነት አሰራር ደንብን ብሎም የድምጽና የምስል ቀረጻ ደንብና አሰራሮችን ስልጠና ወስደዋል።
5/22/2023 • 13 minutes, 59 seconds «እንደ የዶይቸ ቬለ ጋዜጠኛ በስራችን ገለልተኛ ብሎም ሥነ-ምግባሩንም በማክበር ነው» የዶቼ ቬለ ዘጋቢዎች
5/18/2023 • 13 minutes, 59 seconds ከ10ኛዉ ክፍለ ዘመን የጀመረዉ የብሪታንያ ንጉሳዊ ሥርዓት
የብሪታንያ ንጉሳዊ ቤተሰብ በጭራሽ ፖለቲካ ዉስጥ አይገባም። ዘዉድ የሃገሪቱ ባህል የአንድነትና የሃገሪቱ የህልዉና ምልክት ነዉ። ሥነ-ስርዓቱ በጣም አስደሳች ነበር። በታላቅዋ ብሪታንያ ይህ የንጉሳዉያን አስተዳደር ባይኖር ኖሮ፤ ምናልባትም ስኮትላንድ፤ ዌልዝ፤ እንዲሁም ሰሜናዊ አየርላንድ ከብሪታንያ ዉስጥ ከብዙ ዓመታት በፊት በወጡ ነበር።
5/11/2023 • 14 minutes, 57 seconds “ገበታ ለወገኔ” በስዊዘርላን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተሳትፎ
በስዊዘርላንድ ኢትዮጵያዉያንን ያሰባሰበዉ “ገበታ ለወገኔ” የተባለዉ በጎ አድራጎት ድርጅት፤ ስለ ኢትዮጵያ ያገባናል፤ ኃላፊነትም አለብን በሚል መርህ በኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ ከጀመረ ዓመታትን አስቆጥሯል። ለህዝባችን በተለይ ጦርነት ላደቀዉ ህዝብ መድረስ ከማንም በላይ የኛ ኢትዮጵያዉያን ቀዳሚ ኃላፊነት እና ግዴታ ነዉ።
5/4/2023 • 15 minutes, 36 seconds “ገበታ ለወገኔ” በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በጎ አድራጎት
5/4/2023 • 15 minutes, 36 seconds 4/27/2023 • 14 minutes, 4 seconds ፌቼ ጫምባላላ-የሲዳማ ህዝብ የአንድነት ምልክት
ሲዳማ ክልል ህዳር 14 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ከተመሰረተ ዘንድሮ ሁለተኛ ዓመቱን ይዝዋል። የሲዳማ ህዝብ ዘንድሮ የዘመን መለወጫዉን «ፊቼ ጨንበላላ» በተለይ በድምቀት አክብሯል። ህዝቡ ክልሉን ካገኘ ወዲህ ሁሉ ነገር ሆኖለታል፤ ተሳክቶለታል ማለት አይደለም፤ ቢሆንም ግን ህዝቡ በዓሉን በሰላማዊ መንገድ ማክበሩ ትልቅ ነገር ነዉ።
4/27/2023 • 14 minutes, 4 seconds 4/13/2023 • 12 minutes, 47 seconds 4/6/2023 • 13 minutes, 36 seconds 15ኛዉ የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ማን ናቸዉ?
“ባንዲራችንን እንኳን እኛ ግመሎቻችንን ያውቋታል” በሚል አነጋገር የአፋር ህዝቦች ይታወቃሉ። በተለይ በዚህ ንግግራቸዉ የባንዲራን እና የአገር ፍቅርን ይበልጥ የገለፁት 9ኛዉ የአፋር ሱልጣኔት አሊሚራህ ሀንፍሬ ናቸዉ። ልጃቸዉ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ሱልጣን አንፍሬ አሊሚራህ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኃላ 15ኛ ሱልጣን ሆነዉ ተሾመዋል።
3/30/2023 • 14 minutes, 13 seconds «የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ዋርካ ነው የወደቀው» የባህል መድረክ
3/9/2023 • 14 minutes, 9 seconds