አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል
ኢሰመኮ በቅርቡ በመርዓዊ ከተማ በሲቭሎች ላይ በመከላከያ ሠራዊት ከሕግ ውጭ ግድያዎች መፈጸሙን ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጠው መንግሥት የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዓይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም ሲል አስተባብሏል።
2/25/2024 • 39 minutes, 30 seconds አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል
2/25/2024 • 39 minutes, 30 seconds 50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?
የአጼ ኃይለሥላሴን ዘውዳዊ መንግሥት ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት 50 ዓመታት ሞላው። የካቲት 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች እና የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር መላኩ ተገኝ እና ዶ/ር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የአብዮቱ ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
2/18/2024 • 40 minutes, 45 seconds 50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?
የአጼ ኃይለሥላሴ ዘውዳዊ መንግሥትን በማስወገድ የፊውዳላዊ ሥርዓትን ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት የተቀሰቀሰው ከ50 ዓመታት በፊት ነበር። በየካቲት ወር 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች፣ የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ሠራተኞች፣ መምህራን እና ወታደሮች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንገብ በየፊናቸው በዘውዳዊው መንግሥት ላይ ጫና ያደርጉ ነበር። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶክተር መላኩ ተገኝ እና ዶክተር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
2/17/2024 • 40 minutes, 45 seconds እንወያይ፤ በአንድ ላይ ቆመው ለኢትዮጵያ ይጮሁ የነበሩ ወገኖች ዛሬ የት ናቸዉ?
2/4/2024 • 43 minutes, 36 seconds እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሚና ከየት ወዴት?
በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ይታወቃል። አሁን አሁን ግን አብዛኛዉ ዲያስፖራ በዘላቂ የአገሪቱ ጥቅሞች ላይ አንድ ላይ መቆሙ ቀርቶ፤ ተጻራሪና ግዚያዊ የሆኑ የቡድን ፍላጎቶችን ይዞ በየፊናው ቆሞ መታየቱ የተለመደ ሁኗል። ችግሩ ምን ይሆን?
2/4/2024 • 43 minutes, 36 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ
በዓባይ ወንዝ ዉኃ አጠቃቀም ሰበብ ከኢትዮጵያ ጋር የምትወዛገበዉ ግብፅ ደግሞ ለዉጊያም እየተጋበዘች ነዉ።የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚሕ ሽኩሪ ኢትዮጵያን «የአካባቢዉ ያለመረጋጋት ምንጭ» በማለት ወንጅለዋታል።የሐገሪቱ ፕሬዝደንት የቀድሞዉ ፊልድ ማርሻል አብዱልፈታሕ አልሲሲ በበኩላቸዉ ሶማሊያና ደሕንነቷ ላደጋ ከተጋለጠ ግብፅ ጣልቃ ለመግባት
1/28/2024 • 41 minutes, 2 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ
1/26/2024 • 41 minutes, 2 seconds የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የደህንነት ተቋማት ወቅታዊ ሁኔታ
1/21/2024 • 43 minutes, 5 seconds ከውጭና ከሃገር ውስጥ በተሰበሰበ የአገሪቱ ሀብት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት እየተገነቡ ያሉ የመናፈሻዎችና የቤተመንግስት ግንባታዎች፤ በቀጥታ ከመንግስት ካዝና በቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የሚካሄዱ የመንግስት መስሪያቤቶች እድሳት አነጋጋሪነታቸው እንደቀጠለ ነው።
1/7/2024 • 40 minutes, 18 seconds ውይይት፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…የኢትዮጵያ አጣብቂኝ
ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
የኢትዮጵያ አጣብቂኝ፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…?
ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
12/17/2023 • 39 minutes, 33 seconds እንወያይ፤ በአማራ ክልል የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማቆምያዉ የት ነዉ?
ለአማራ ክልሉ ሰብዓዊ ቀዉስ ተጠያቂዉ ማን ነዉ? በትግራይ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተገድለዋል። አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ የተኩስ አቁም ታዉጆ ዉይይት መጀመር አለበት» ይላሉ ተወያዮች እርሶስ?። እርሶስ? ይጻፉልን!
12/10/2023 • 43 minutes, 15 seconds 11/26/2023 • 40 minutes, 22 seconds የሰላም ንግግሩ ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ
ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎቹ ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው።
11/19/2023 • 43 minutes, 41 seconds መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የሚያደርገው የሰላም ንግግር ዘላቂ ሰላም ያመጣ ይሆን ?
11/19/2023 • 43 minutes, 41 seconds ከምንም በላይ ሕጻናት፤ ሴቶችና አረጋውያን ተጎጂዎች ናቸው
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች
11/5/2023 • 36 minutes, 28 seconds በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶችት ጥሰቶች
ድንገት ተፈናቅለው በወጡበት የቀሩ ፣በማያውቁትና መጠለያ ሊባሉ በማይችሉ ስፍራዎች ለብዙ ጊዜያት የቆዩ በርካቶች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ችግሮቻቸው እየተባባሱ እንጂ እየቀነሱ አልሄዱም። በመጠለያ ጣቢያዎች ለከፋ ችግር ከተጋለጡት አብዛኛዎቹ ምርጫ በማጣታቸው ወደ ቀድሞው ቀያቸው ለመመለስ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ሆኖም የጸጥታ ስጋት አላቸው።
11/5/2023 • 36 minutes, 28 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብርና አሰራር
10/27/2023 • 39 minutes, 51 seconds እንወያይ፤ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደቁ የተባሉበት አሳሳቢዉ ዉጤትና አንደምታዉ
ከ 800 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ ብቻ ሳይሆን፤ በችግር ያስተማሩ ወላጆች ብሎም በህብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ቀላል አለመሆኑ ነዉ። የችግሩ መንስኤ ምንድነው? የትምህርት ስርዓት ዉድቀት? ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ለከፍተኛ ተቋማት በቁ፤ ብዙኃኑ ግን ወድቋል፤ የተባለለበትን ፈተና የወደቀዉ ማነዉ? እንዴት ትገመግሙታላችሁ? ጻፉልን!
10/22/2023 • 39 minutes, 41 seconds በተስፋ የተሞሉ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ የተሰማበት ዜና፤ በኑሮ ዉድነት በቀዉስ ብሎም ከጦርነት ወጥታ ወደ ሌላ ጦርነት ለገባችዉ ሃገር ኢትዮጵያ ሌላ እራስ ምታት ነዉ። ሃላፊነቱን ማን ይዉሰድ?
10/22/2023 • 39 minutes, 41 seconds ውይይት፦ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚሽን ሥራ መቋረጥ ምን ያጎድላል?
10/15/2023 • 40 minutes, 3 seconds ያለተጠያቂነት እየተባባሰ የመጣው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
10/9/2023 • 39 minutes, 48 seconds «በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሰብአዊ መብት አንጻር እንዴት ይታያል?»
በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች የሚኖሩባቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከኢንተርኔቱ ዓለም እንዳይገናኙ ከተዘጋባቸው ሰነባብተዋል ። ሌላው ቀርቶ የቀጥታ ስልክ መስመር አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች እና ከተሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። በኢትዮጵያ አንዳች ነገር ኮሽ ሲል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ ሲቋረጥ ይስተዋላል ።
9/24/2023 • 40 minutes, 4 seconds አዲሱ ዓመት ለተቀጣሪው ሰራተኛ ተስፋ ወይስ ስጋት ?
በሀገሪቱ በተለይ የመሰረታዊ ፍጆታ ቁሶች እና የቤት ኪራይ በየጊዜው ያለከልካይ እጅግ በተጋነነ ሁኔታ ጭማሪ ሲያሳዩ ሰራተኛው በወር በሚያገኘው ደመወዝ ላይ ጭማሪ ስለመደረጉ ብዙም አይሰማም ወይም ቢኖርም ያለውን የገበያ እና የኑሮ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘቱ ነው የሚነገረው ።
9/17/2023 • 45 minutes, 28 seconds በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ተቀጣሪ የህብረተሰብ ክፍል ተስፋው ምን ይሆን?
9/17/2023 • 45 minutes, 28 seconds 2015 ግጭቶች የተካሄዱበት፣ የመንግሥት ተባባሪ የነበሩ ውጊያ የገጠሙበት ፣ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የደረሰበት ፣ቤቶች የፈረሱበት ሰዎች የተፈናቀሉበት፣ የኑሮ ውድነት እጅግ የናረበት ጋዜጠኞች የታሰሩበት ኢንተርኔትም የተቋረጠበት ዓመት ነበር። እነዚህ ችግሮች ወደ 2016 ዓም እንዳይሻገሩ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?
9/10/2023 • 41 minutes, 41 seconds የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋን
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸው ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለመሆኑ ይህ ምን ያህል የመገናኛ አውታሮች ሽፋን አገኘ?
8/27/2023 • 39 minutes, 54 seconds እንወያይ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያመጣ ይሆን?
ተወያዮች፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተፈጥሮዉ መብት ገዳቢ ነዉ፤ኢትዮጵያም ተሞክሮ ይህንኑ ያሳያል። መንግሥትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዝም ያለዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ ለሰላም ወደ ድርድር እንዲመጡ፤ጦርነትም ይቁም ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።መንግሥት የጅምላ እስሩን ያቁም፤የአማራ ክልልን ጥያቄዎች ይመልስ ብለዋል። እርሶስ? አስተያየት አሎት?
8/21/2023 • 42 minutes, 47 seconds የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያሰፍን ይሆን? የክልሉን ጥያቄዎችስ ይፈታ ይሆን?
8/20/2023 • 42 minutes, 47 seconds ውይይት፦ የአማራ ክልል ቀውስ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ
8/15/2023 • 39 minutes, 58 seconds የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ
በአማራ ክልል ሲብላላ የቆየው ቅራኔ በሣምንቱ መጀመሪያ ወደ ውጊያ ቢያመራም የመረጋጋት ዝንባሌ አሳይቷል። የቀውሱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው? በውይይት ካልተቋጨ በአማራ ክልል እና በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ዳፋ ምን ሊሆን ይችላል? ዶክተር ታደሰ ጥሩነህ፣ ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል።
8/14/2023 • 39 minutes, 58 seconds የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ተስፋ እና ስጋት
7/30/2023 • 40 minutes, 9 seconds 7/2/2023 • 40 minutes, 40 seconds ውይይት፦ የዎላይታ ሕዝበ-ውሳኔ እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ
6/25/2023 • 38 minutes, 32 seconds 6/4/2023 • 39 minutes, 59 seconds 5/28/2023 • 41 minutes, 55 seconds እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ከግጭትና ቀዉስ አዙሪት እንዴት ትዉጣ?
በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?
5/28/2023 • 41 minutes, 55 seconds አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ
5/14/2023 • 40 minutes, 20 seconds እንወያይ፦ የሸገር ከተማ አስተዳደር ቤት ፈረሳ እና ውዝግቡ
4/23/2023 • 40 minutes, 42 seconds የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ እና አንድምታው
4/16/2023 • 42 minutes, 47 seconds የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ
በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? ሳምንታዊ እንወያይ መሰናዶ።
4/9/2023 • 40 minutes, 36 seconds ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች? የፍትህ ሚኒስቴር ካቋቋመው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ እና ዶ/ር ማርሸት ታደሰ፤ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የሰብዓዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና ዘ-ሔግ በሚገኝ ፍርድ ቤት በአማካሪነት የሚሰሩት አቶ ካሳሁን ሞላ በውይይቱ ተሳትፈዋል
3/26/2023 • 43 minutes, 38 seconds ውይይት፦ ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች?
3/26/2023 • 43 minutes, 38 seconds ዉይይት፤ የፕሪቶርያዉ ስምምነት በርግጥ ተፈጻሚ እየሆነ ነዉ?
ፕሪቶርያ ላይ በሰላም ስምምነት ከተቋጨ አራት ወር የሆነዉና አስከፊ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመበት የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ቢያበቃም ብዙዎች በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ጥርጣሬ አላቸዉ። መንግሥት ስምምነቱን እያስፈጸመ አይደለም፤ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ህወሓት ሁሉን አካታች የሆነ ሽግግር መንግሥት ለመመስረት አልቻለም፤ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።
3/20/2023 • 42 minutes, 33 seconds የፕሪቶርያዉ የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት በምን ደረጃ ላይ ነዉ? የፌደራል መንግሥት እና ህወሓትስ ምን ተወያዩ? ምንስ ተስማማ?
3/19/2023 • 42 minutes, 33 seconds 3/12/2023 • 38 minutes, 44 seconds የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ወዴት እያመራ ነው?
2/26/2023 • 40 minutes, 1 second ሶስት ሕዝበ-ውሳኔዎች፤ አራት ክልሎች፦ የደቡብ ጥያቄ ተመለሰ?
2/13/2023 • 40 minutes, 25 seconds የአዲስ አበባ የተጨማሪ ቋንቋ ስርዓተ ትምሕርት አተገባበርና ትችቱ
1/22/2023 • 39 minutes, 37 seconds የአዲስ አበባ የአንደኛ ደረጃ የተጨማሪ ቋንቋ ስርዓተ ትምሕርት አተገባበርና ትችቱ
ተማሪዎች ተጨማሪ የአገር ውስጥ ቋንቋ እንዲማሩ የሚያደርገውን ውሳኔ ጠቀሚ ሲሉ የደገፉት እንዳሉ ሁሉ በጥድፍያ የተከናወነና ፖለቲካዊ ጫናም ያረፈበት ነው በማለት የተቹትም አሉ። የከተማዋ ነዋሪ በጉዳዩ ላይ በቂ ውይይት አላካሄደም የትምሕርቱም አዋጭነት በሙከራ ደረጃ ሳይፈተሽ ተግባራዊ መሆኑ አግባብ አይደለም የሚሉና የመሳሳሉ ትችቶችም ቀርበውበታል
1/22/2023 • 39 minutes, 37 seconds መንግሥት ካጠፋን ቆንጥ ጡን ብሏል? በሰላሙ ጥረት ማህበረሰቡ እንዲነጋገር ለምን መድረክ አልተሰጠዉም?
1/15/2023 • 40 minutes, 44 seconds ዉይይት፤ የኢትዮጵያዉያን ማህበራዊ መስተጋብር እንዴት ይመለስ?
የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት እርቅ ሲፈፅሙ በጦርነት ዉስጥ የነበረዉ ማኅበረሰብ እፎይ ይበል እንጂ ማኅበረሰቡ ለዘመናት አብሮት ከኖረዉ ህዝብ ጋር አሁንም እንደተራራቀ ነዉ። የሁለት ዓመቱ የእርስ በርስ ጦርነት በማኅበራዊ መ ስተጋብሩ ላይ ከፍተኛ ጠባሳን ጥሎ ነዉ ያለፈዉ። በህብረተሰቡ ውስጥ እውነተኛ እርቅና ይቅርታ እንዲመጣ ምን መደረግ አለበት?
1/15/2023 • 40 minutes, 44 seconds ወጣቶቹን የሚያረግፈው ስደት፦ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ
በጥቅምት እና ሕዳር ወራት ከ50 በላይ የኢትዮጵያውያን አስከሬኖች በማላዊ እና በዛምቢያ ተገኝተዋል። በየአገራቱ የተካሔዱ ምርመራዎች በመንገድ ላይ ሞተው የተገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ በማምራት ላይ እንደነበሩ የሚጠቁሙ ናቸው። ይኸ ውይይት የጉዞ መስመሩን ጠባይ፣ የስደቱን ገፊ ምክንያቶች እና የኢትዮጵያውያኑን መከራ የሚመረምር ነው።
1/3/2023 • 41 minutes, 44 seconds ውይይት፤ ወጣቶቹን የሚያረግፈው ስደት፦ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ
1/1/2023 • 41 minutes, 44 seconds የመገናኛ አውታሮች ሁለት ገጽታ በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ አንዳንድ የመገናኛ አውታሮች በጥቃት አድራሾች ሊድበሰበሱና ሊዳፈኑ ይችሉ የነበሩ የግፍ ተግባራትን፣ ግድያዎችን፤ አላግባብ እስሮችንና ሌሎች በደሎችን በማጋለጥ በተለይ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ ይታያል። ግድያ፤ ጭፍጨፋና ማፈናቀሎችን የሚያስፋፉ አደገኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በብርቱ የሚተቹም አሉ። ውይይት
ተወያዮች «በመንግሥት በኩል ያለዉ ዝምታ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተቸግረናል።»
12/11/2022 • 42 minutes, 10 seconds ዉይይት፤ ስንቱ ሲሞት ነዉ በኢትዮጵያ መግደልና መገዳደል የሚቆመዉ?
ሰሜን ኢትዮጵያ ይካሄድ የነበረዉ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቆሙ የፈጠረዉ ስሜት ሳይቀዘቅዝ፤ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብሔርን መሰረት ያደረገዉ ግጭትና ጥቃት አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለያዩ የወለጋ ዘኖች አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ባነጣጠረዉ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በየአካባቢዉ እየተሰቃዩ ነዉ።
12/11/2022 • 42 minutes, 10 seconds የኢትዮጵያ "ደህንነት ተግዳሮት" የተባለው "የተደራጀ ሌብነት" በኮሚቴ ሥራ ይቆማል?
የኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ እና የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ባልደረቦችን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩ ሹማምንት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። በጸረ-ሙስና ዘመቻው የጸጥታ፣ የፍትኅና የመሬት አስተዳደር ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል። የጸረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ የአገር ደህንነት ሥጋት የተባለውን ሙስና ማቆም ይችላል?
12/4/2022 • 40 minutes, 28 seconds ውይይት፦ የኢትዮጵያ "ደህንነት ተግዳሮት" የተባለው "የተደራጀ ሌብነት" በኮሚቴ ሥራ ይቆማል?
12/4/2022 • 40 minutes, 28 seconds የህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም የእንወያይ ዝግጅት
11/20/2022 • 40 minutes, 50 seconds የትጥቅ መፍታት እና የመከላከያ ያልሆኑ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት አንድምታ
ግጭት ጦርነቱ ቆሞ ሰላም እንዲወርድ ችግሮች በንግግር ይፈቱ ዘንድ ይወተውቱ የነበሩቱ አሁን ስምምነቱን በደስታ ከመቀበል ባሻገር አሁን ጥያቄው ስምምነቱ በእርግጥ ተግባራዊ ይሆን የሚለው ሆኗል።
11/20/2022 • 40 minutes, 50 seconds ቃለ መጠይቅ ከፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጋር
11/15/2022 • 24 minutes, 56 seconds ዘላቂ መፍትኄ የሚሻው የፀጥታ ስጋት በኦሮሚያ ክልል
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መደረጉን በርካቶች በበጎ ጎኑ ቢቀበሉትም በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ግን ሌሎች ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎችም ሰላማዊ መፍትኄ እንዲፈለግ ተደጋጋሚ ጥሪ ይሰማል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር እጅግ መባባሱ መነጋገሪያ ኾኗል።
11/13/2022 • 38 minutes, 7 seconds በኦሮሚያ ክልል የፀጥታው ችግር ከሰሞኑ ተባብሶ ቀጥሏል
11/13/2022 • 38 minutes, 7 seconds 11/6/2022 • 36 minutes, 28 seconds ዉይይት፤ በጦርነት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ የታጀበዉ የሰላም ድርድር
„የሰላም ንግግሩ ጠረቤዛ ጠባብ ነዉ። ችግሩ በጦርነት ላይፈታ ለምን ሰዉ ያልቃል፤ አገር ይወድማል? ህብረተሰቡ መራብ፤ መገደል፤ ተስፋ መቁረጥ ይብቃን ብሎ መንቃት አለበት ። እነዚህ ቡድኖች የሚወዛገቡበት ችግር የጎበዝ አለቃ አይነት ክርክር ነዉ። ከዉይይቱ በፊት ተኩስ ማቆም ግዳጅ መሆ ን ነበረበት። የኤርትራ ሰራዊት በቀላሉ ይወጣልስ?“
10/30/2022 • 40 minutes, 43 seconds ዉይይት፤ በጦርነት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ የታጀበዉ የሰላም ድርድር
10/30/2022 • 40 minutes, 43 seconds የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ችግሮችና አስተምህሮቱ
10/23/2022 • 39 minutes, 33 seconds የ2014 ዓ.ም. 12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ችግሮችና አስተምህሮቱ
ባለፈው ሳምንት ፣በአራት የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ለመፈተን ከሄዱ ተማሪዎች ፈተናውን ጥለው ወጡ የተባሉ ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ዳግም ፈተና እንዳይወስዱ ትምሕርት ሚኒስቴር መወሰኑ ሲያነጋግር ከርሟል። የፈተናው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና አስተምህሮቱ የዚህ ውይይት ትኩረት ነው።
10/23/2022 • 39 minutes, 33 seconds ድርድሩ መክሸፍ፣ ዉጊያዉና የድርድር ባሕል
10/16/2022 • 41 minutes, 59 seconds የዋጋ ንረት፦ ገፊ ምክንያቶች፣ የብሔራዊ ባንክ እርምጃ እና የወደፊት ሥጋቶች
10/9/2022 • 39 minutes, 21 seconds የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና የጎረቤት ሃገራት ሚና
ሰላማዊ መፍትሔ ያጣው የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ጨምሮ ሀገሪቱን ለሚያብጠው አለመረጋጋት በጦርነቱ በቀጥታ በመሳተፍም ሆነ ግጭቶች እንዲባባሱ የጎረቤት ሃገራት ሚና እንዳላቸው በስም እየተጠቀሰ ሲነገር ይሰማል። ድርድን በመደገፍ ለሰላም ንግግሩ ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው የገለጹ የጎረቤት ሃገራት እንዳሉ ስማቸው ይጠቀሳል።
10/2/2022 • 38 minutes, 37 seconds እንወያይ፦ ያለመተማመን፤ የሰላም ውይይት እንቅፋት
9/25/2022 • 39 minutes, 17 seconds ኢትዮጵያ፦ በግጭት ጦርነቱ የሰላማዊ ዜጎች መብት ጥሰት
ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት ጦርነቱ የተነሳ ሰላማዊ ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ሲገደሉ፤ ጥቃት ሲደርስባቸው እና በገፍ ሲፈናቀሉ ይታያል። በግጭት ጦርነቶች ወቅት የሰላማዊ ዜጎች የሰብአዊ መብት አጠባበቅ» ምን ይመስላል? የሰብአዊ መብት ተሟጋች ባለሞያዎችን ለውይይት ጋብዘናል። ሙሉው ውይይት ከታች በድምፅ ይገኛል።
9/11/2022 • 39 minutes, 41 seconds «ማጠንጠኛው ተጠያቂነት ነው» የእንወያይ መሰናዶ
9/11/2022 • 39 minutes, 41 seconds የኢትዮጵያ ፖለቲካ ክሽፈትና ዳግም ያገረሸዉ ጦርነት
9/4/2022 • 39 minutes, 58 seconds